በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 128

እስከ መጨረሻው መጽናት

ኦዲዮ ምረጥ
እስከ መጨረሻው መጽናት
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ማቴዎስ 24:13)

 1. 1. ለመጽናት ምክንያት ይሆናል፣

  አምላክ የገባው ቃል።

  አንተን የማረከህ እውነት

  ነው እምነት ’ሚጣልበት።

  ያምላክን ቀን እይ አቅርበህ፤

  ጸንተህ ኑር በእምነትህ።

  በታማኝነት ስትጸና

  ያጠራሃል ፈተና።

 2. 2. የቀድሞ ፍቅርህን ጠብቅ፤

  ስለሚችል ላይዘልቅ።

  ፈተናው ከባድ ቢሆንም

  ተወጣው እንደምንም።

  ችግር ሲደራረብብህ

  ጥርጣሬ አይግባህ።

  አምላክ መውጫ ያዘጋጃል፤

  ‘አይዞህ፣ አለሁ’ ይልሃል።

 3.  3. እስከ ፍጻሜው ’ሚጸኑ

  ሁሉ ይድናሉ።

  ባምላክ የሕይወት መጻፍ ላይ

  በደማቅ ይጻፋሉ።

  ጸንቶ መቆም ግብህ ይሁን፤

  ጽናት ይሥራ ሥራውን።

  አምላክ ሞገስ ይሰጥሃል፤

  ደስተኛ ያደርግሃል።

(በተጨማሪም ዕብ. 6:19ን፣ ያዕ. 1:4ን፣ 2 ጴጥ. 3:12ን እና ራእይ 2:4ን አንብብ።)