በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 118

“እምነት ጨምርልን”

ኦዲዮ ምረጥ
“እምነት ጨምርልን”
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ሉቃስ 17:5)

 1. 1. አምላክ ሆይ፣ ፍጹም ባለመሆናችን፣

  ወደ ክፋት ያደላል ልባችን።

  ይሖዋ ሆይ፣ ባንተ ላይ እምነት ማጣት፣

  ነው ሳናውቀው የሚያጠምደን ኃጢያት።

  (አዝማች)

  ይሖዋ ሆይ፣ እምነትን ጨምርልን።

  ታውቀዋለህ የሚያስፈልገንን።

  መሐሪ ነህ፤ እምነትን ጨምርልን።

  እናክብርህ በቃል፣ በሥራችን።

 2. 2. ያለ’ምነት ሊያስደስትህ ’ሚችል ማነው?

  አንርሳ እምነት ወሮታ ’ንዳለው።

  ምን ይመጣ ይሆን ብለን አንሰጋም፤

  የ’ምነት ጋሻ ስላለን አንፈራም።

  (አዝማች)

  ይሖዋ ሆይ፣ እምነትን ጨምርልን።

  ታውቀዋለህ የሚያስፈልገንን።

  መሐሪ ነህ፤ እምነትን ጨምርልን።

  እናክብርህ በቃል፣ በሥራችን።

(በተጨማሪም ዘፍ. 8:21ን፣ ዕብ. 11:6ን እና 12:1ን ተመልከት።)