በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 115

አምላክ ላሳየን ትዕግሥት አመስጋኝ መሆን

ኦዲዮ ምረጥ
አምላክ ላሳየን ትዕግሥት አመስጋኝ መሆን
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(2 ጴጥሮስ 3:15)

 1. 1. አምላካችን፣ ታላቅ ነው ኃይልህ፤

  ጽድቅን እጅግ ትወዳለህ።

  ግን በምድር ክፋት ነግሷል፤

  ልባችንም በጣም አዝኗል።

  አትዘገይም፣ ለሰው ባይመስልም፤

  ክፋት ይጠፋል፤ ጊዜው ቀርቧል።

  (አዝማች)

  አንተን ተስፋ ’ናደርጋለን፤

  ስምህንም እናውጃለን።

 2. 2. እናውቃለን ሺህ ዓመት ላንተ፤

  እንዳንድ ቀን እንደሆነ።

  ታላቁ ቀንህ ይመጣል፤

  አይዘገይም፣ ጊዜው ቀርቧል።

  ኃጢያትን ሁሉ ብትጠላም፣

  ሰው ሲመለስ ግን ደስ ይልሃል።

  (አዝማች)

  አንተን ተስፋ ’ናደርጋለን፤

  ስምህንም እናውጃለን።

(በተጨማሪም ነህ. 9:30ን፣ ሉቃስ 15:7ን እና 2 ጴጥ. 3:8, 9ን ተመልከት።)