በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 96

የአምላክ መጽሐፍ ውድ ሀብት ነው

ኦዲዮ ምረጥ
የአምላክ መጽሐፍ ውድ ሀብት ነው
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ምሳሌ 2:1)

 1. 1. በእውቀት የተሞላ መጽሐፍ አለ፤

  ሰላምን፣ ደስታን፣ ተስፋን ያዘለ።

  ሐሳቦቹ ግሩም፣ ኃይልም ያላቸው፤

  ብርሃን፣ ሕይወት የሚሰጡ ናቸው።

  መጽሐፍ ቅዱስ ነው ይህ አስደናቂ ሀብት።

  ጸሐፊዎቹን አምላክ መራቸው፤

  ይሖዋን ይወዳሉ ከልባቸው፤

  ያምላክ መንፈስ ነው ያነሳሳቸው።

 2. 2. ስላምላክ ፍጥረት ጻፉ እውነታውን፤

  ጽንፋለም የ’ጁ ሥራ መሆኑን።

  ሰው ሲፈጠር ፍጹም መሆኑን ጻፉ፤

  በኋላም ከገነት መባረሩን።

  ተርከዋል አንድ መልአክ የሠራውን፤

  ያምላክን ሥልጣን መገዳደሩን።

  ይህም ኃጢያትና ሐዘን አምጥቷል፤

  በቅርቡ ግን አምላክ ድል ያደርጋል።

 3.  3. ዛሬ ደስታችን እጥፍ ድርብ ሆኗል፤

  የአምላክ መንግሥት መግዛት ጀምሯል።

  ለሰው ሁሉ እንስበክ ምሥራቹን፤

  በስፋት እናውጅ በረከቱን።

  በዚህ መጽሐፍ ነው ይህንን ያወቅነው፤

  በ’ርግጥም ቃሉ አስደናቂ ነው።

  ስናነበው ልባችን ይረጋጋል፤

  ሕያው መጽሐፍ ነው፤ መንፈስ ያድሳል።

(በተጨማሪም 2 ጢሞ. 3:16ን እና 2 ጴጥ. 1:21ን ተመልከት።)