በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 95

ብርሃኑ እየደመቀ ነው

ኦዲዮ ምረጥ
ብርሃኑ እየደመቀ ነው
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ምሳሌ 4:18)

 1. 1. የጥንት ነቢያት ማወቅ ጓጉተው ነበር፣

  ፍጥረትን ስለሚያድነው ዘር።

  መንፈስ ገለጸ መሲሕ ’ንደሚመጣ፣

  የሰውን ዘር ነፃ ሊያወጣ።

  አሁን ጊዜው ደርሶ መሲሑ ነግሷል፤

  መገኘቱ ይፋ ሆኗል።

  ይህን ማወቃችን ታላቅ ክብር ነው፤

  መላ’ክት ሳይቀር የጓጉለት ነው።

  (አዝማች)

  ድምቀት ጨምሯል መንገዳችን፤

  እንደ ቀትር ብርሃን ሆኗል።

  አምላክ እውቀት ይገልጥልናል፤

  በመንገዱ ይመራናል።

 2. 2. ጌታችን፣ ታማኝ ባሪያ ሾሞልናል፤

  በወቅቱ ምግብ ይሰጠናል።

  የ’ውነት ብርሃን እየደመቀ ሄዷል፤

  ማራኪና አሳማኝ ሆኗል።

  መንገዱ ጠርቷል አንደናቀፍም፤

  በብርሃኑ ’ንጓዛለን።

  ይመስገን አምላክ የ’ውነት ምንጭ የሆነው፤

  በደስታ እንጓዝ አብረነው።

  (አዝማች)

  ድምቀት ጨምሯል መንገዳችን፤

  እንደ ቀትር ብርሃን ሆኗል።

  አምላክ እውቀት ይገልጥልናል፤

  በመንገዱ ይመራናል።

(በተጨማሪም ሮም 8:22ን፣ 1 ቆሮ. 2:10ን እና 1 ጴጥ. 1:12ን ተመልከት።)