በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 89

ስማ፣ ታዘዝ፤ ትባረካለህ

ኦዲዮ ምረጥ
ስማ፣ ታዘዝ፤ ትባረካለህ
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ሉቃስ 11:28)

 1. 1. ክርስቶስን ሰምተን ስንታዘዘው፣

  ትምህርቶቹ ብርሃን ይሆኑናል።

  መስማትና ማወቅ ያስደስተናል፤

  መታዘዝ ግን በረከት ያስገኛል።

  (አዝማች)

  አምላክ ፈቃዱን ሲገልጽ፣

  ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

  ወዳምላክ እረፍት መግባት ከፈለግክ፣

  ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

 2. 2. በዓለት ላይ የተመሠረተ ቤት፣

  ለሰው ከለላ ’ንደሚሆንለት፣

  የኢየሱስን ትምህርቶች መከተል፣

  ሕይወታችንን ይጠብቀዋል።

  (አዝማች)

  አምላክ ፈቃዱን ሲገልጽ፣

  ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

  ወዳምላክ እረፍት መግባት ከፈለግክ፣

  ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

 3. 3. በጅረቶች ዳር የተተከለ ዛፍ፣

  በየወቅቱ ፍሬ እንደሚሰጥ፣

  እንደ ልጆቹ አምላክን ብንሰማው፣

  ይሰጠናል የዘላለም ሕይወት።

  (አዝማች)

  አምላክ ፈቃዱን ሲገልጽ፣

  ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

  ወዳምላክ እረፍት መግባት ከፈለግክ፣

  ስማ፣ ታዘዝ፤ ተባረክ።

(በተጨማሪም ዘዳ. 28:2ን፣ መዝ. 1:3ን፣ ምሳሌ 10:22ን፣ ማቴ. 7:24-27ን እና ሉቃስ 6:47-49ን ተመልከት።)