እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(መዝሙር 91)

 1. 1. ይሖዋ መጠጊያችን፤

  ጽኑ መከታችን።

  እንኑር ተረጋግተን፤

  በጥላው ሥር ሆነን።

  ታማኞቹን ይታደጋል፤

  እናውቃለን ያድነናል።

  ታማኝ ነው አምላካችን፤

  ይሆናል መሸሸጊያችን።

 2. 2. ጎናችን ሺ ቢወድቁም፣

  ብዙ ሰዎች ቢያልቁም፣

  ቅኖች ግን ይድናሉ፤

  ጻድቃን ይተርፋሉ።

  ጥፋት እኛ ጋ አይቀርብም፤

  አንፈራም፣ አንሸበርም።

  አምላክ ይጠብቀናል፤

  በክንፉም ይከልለናል።

 3. 3. በመንገድ ካለ ወጥመድ፣

  አምላክ ያድነናል።

  ፍላጻው አይጎዳንም፤

  ጥፋት አይነካንም።

  የሚያስፈራን ነገር የለም፤

  ምንም አያሸብረንም።

  ይሖዋ መጠጊያችን፤

  የዘላለም ጠባቂያችን።

(በተጨማሪም መዝ. 97:10፤ 121:3, 5ን እና ኢሳ. 52:12ን ተመልከት።)