በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 74

የመንግሥቱን መዝሙር ዘምሩ!

ኦዲዮ ምረጥ
የመንግሥቱን መዝሙር ዘምሩ!
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(መዝሙር 98:1)

 1. 1. ይህ መዝሙር ነው የደስታ የድል መዝሙር፤

  ለይሖዋ ውዳሴ ’ሚጨምር።

  ብሩህ ተስፋ ይሰጣሉ ቃላቱ፤

  እንዘምር ይሄ ነው መል’ክቱ፦

  (አዝማች)

  ‘ዙፋኑ ፊት ኑ! አምልኩት፤

  ልጁ ነግሷል፤ አውጁለት!

  የመንግሥቱን መዝሙር ኑና ተማሩ።

  ስገዱለት፤ ስሙንም አክብሩ።’

 2. 2. ባዲስ መዝሙር መንግሥቱን ’ናውጃለን።

  ’የሱስ ነግሷል፤ ምድርንም ይገዛል።

  አዲስ ብሔር ተወልዷል እንደ ቃሉ፤

  ቅቡዓኑም በደስታ ይላሉ፦

  (አዝማች)

  ‘ዙፋኑ ፊት ኑ! አምልኩት፤

  ልጁ ነግሷል፤ አውጁለት!

  የመንግሥቱን መዝሙር ኑና ተማሩ።

  ስገዱለት፤ ስሙንም አክብሩ።’

 3. 3. ይሄ መዝሙር ቀላል ነው ለትሑታን።

  መል’ክቱ ግልጽ፣ የሚነካ ልብን።

  ባለም ዙሪያ ብዙዎች አውቀውታል፤

  ራሳቸውም ሌሎችን ጋብዘዋል፦

  (አዝማች)

  ‘ዙፋኑ ፊት ኑ! አምልኩት፤

  ልጁ ነግሷል፤ አውጁለት!

  የመንግሥቱን መዝሙር ኑና ተማሩ።

  ስገዱለት፤ ስሙንም አክብሩ።’

(በተጨማሪም መዝ. 95:6ን፣ 1 ጴጥ. 2:9, 10ን እና ራእይ 12:10ን ተመልከት።)