በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 62

አዲሱ መዝሙር

ኦዲዮ ምረጥ
አዲሱ መዝሙር
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(መዝሙር 98)

 1. 1. ዘምሩ ላምላክ፤ አዲስ የውዳሴ መዝሙር።

  አውሩ፣ ተናገሩ የሱን ታላቅ ተግባር።

  ድል አድራጊ ነው፤ ኃያል ክንዱን አሳይቷል።

  ፍትሕን ይወዳል፤

  በጽድቅም ይፈርዳል።

  (አዝማች)

  ዘምሩ!

  አዲሱን ዝማሬ!

  ዘምሩ!

  ያህ ንጉሥ ነው ሁሌ!

 2. 2. ለንጉሣችን እንዘምርለት በደስታ!

  ስሙን አወድሱ፤ ከፍ አ’ርጉት በ’ልልታ።

  ሕዝቦቹ ሁሉ ላምላክ በኅብረት ዘምሩ።

  መለከት፣ በገናም

  ያህን ያመስግኑ።

  (አዝማች)

  ዘምሩ!

  አዲሱን ዝማሬ!

  ዘምሩ!

  ያህ ንጉሥ ነው ሁሌ!

 3. 3. ባሕሮችና በውስጣቸው ያለው ሕይወት፣

  የምድርም ፍጥረታት እሱን ያወድሱት።

  ምድርም ሐሴት ታ’ርግ፤ ወንዞች ሁሉ ያጨብጭቡ።

  ተራሮች፣ ኮረብቶች

  ክብሩን ያስተጋቡ።

  (አዝማች)

  ዘምሩ!

  አዲሱን ዝማሬ!

  ዘምሩ!

  ያህ ንጉሥ ነው ሁሌ!

(በተጨማሪም መዝ. 96:1፤ 149:1ን እና ኢሳ. 42:10ን ተመልከት።)