እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ሉቃስ 10:6)

 1. 1. ‘እውነት ይታወጅ’ ብሏል ኢየሱስ።

  ቃሉን ሰብኳል በየቦታው፤

  ሙቀት፣ ፀሐይ ሳይበግረው።

  ለአምላክ በጎች ፍቅር ስላለው፣

  ጠዋት፣ ማታ ይጓዝ ነበር

  በሁሉም ቦታ።

  በመንገድ ላይ፣ በየቤቱ፣

  እንናገር ለሰው ሁሉ፤

  ሥቃይ፣ ችግር ይወገዳል በቅርቡ።

  (አዝማች)

  ባለም ዙሪያ፣

  ሰላም ወዳዶችን ፍለጋ፣

  ባለም ዙሪያ፣

  ቅን ልብ ያላቸውን ፍለጋ፣

  እንሄዳለን

  ሁሉም ሰው ጋ።

 2.  2. ጊዜው ይነጉዳል፤ በፍጥነት ያልፋል።

  ለመታደግ ከስንት አንዱን

  ብርቱ ጥረት ያስፈልጋል።

  ፍቅር ስላለን ተስፋ አንቆርጥም፣

  ከመፈለግ

  ልባቸው የተሰበረውን።

  በገጠርም፣ በከተማ፣

  ሰው ስናገኝ የሚሰማ፣

  ያኔ ልባችን ይሞላል በደስታ።

  (አዝማች)

  ባለም ዙሪያ፣

  ሰላም ወዳዶችን ፍለጋ፣

  ባለም ዙሪያ፣

  ቅን ልብ ያላቸውን ፍለጋ፣

  እንሄዳለን

  ሁሉም ሰው ጋ።

(በተጨማሪም ኢሳ. 52:7ን፣ ማቴ. 28:19, 20ን፣ ሉቃስ 8:1ን እና ሮም 10:10ን ተመልከት።)