እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ሚክያስ 6:8)

 1. 1. አባታችን መብቱን ሰጠን፤

  እጁን ይዘን ለመሄድ አብረን።

  ታማኝ ፍቅሩ ወደር የለው፤

  ጎዳናውን ለሚፈልግ ሰው።

  መንገዱን አመቻቸልን፤

  አብረነው መሄድ ቻልን።

  ለሱ ልንኖር ወሰንን፤

  ልንሰጠው ሕይወታችንን።

 2. 2. ባለንበት በዚህ ዘመን፣

  መጨረሻው በቀረበበት፣

  መከራ ይደርስብናል፤

  ከባድ ስደት ያጋጥመናል።

  አምላክ ግን ይጠብቀናል፤

  እሱን መያዝ ይበጃል።

  እናምልከው ለዘላለም፤

  ታማኝ በመሆን ምንጊዜም።

 3. 3. አምላካችን ይረዳናል፤

  በመንፈሱ፣ በቃሉ በኩል።

  በጉባኤም ያንጸናል፤

  ወደሱ ስንጸልይ ይሰማል።

  እሱን ለማስደሰት ስንጥር

  ብርታት፣ ኃይል ’ናገኛለን።

  ባምላካችን በመታመን

  ታማኝ ሆነን እንኖራለን።

(በተጨማሪም ዘፍ. 5:24፤ 6:9ን እና 1 ነገ. 2:3, 4ን ተመልከት።)