መዝሙር 37
ይሖዋን በሙሉ ነፍስ ማገልገል
ኦዲዮ ምረጥ
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል
1. ይሖዋ ሆይ፣ ሉዓላዊው፣
አንተን ልውደድህ፣ ላገልግልህ።
ላንተ ልደር በሙሉ ነፍስ፤
በየ’ለቱ አንተን ላወድስ።
ሕግጋትህን አከብራለሁ፤
ት’ዛዛትህን ’ወዳለሁ።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ ይገባሃል፤
በሙሉ ነፍስ አንተን ላገልግል።
2. ፀሐይ፣ ጨረቃና ምድር፣
ይናገራሉ ያንተን ክብር።
እኔም እመሠክራለሁ፤
ቅዱስ ስምህን አውጃለሁ።
ላገለግልህ ወስኛለሁ፣
ሕይወቴን ሰጥቼሃለሁ።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ፣ ይገባሃል፤
በሙሉ ነፍስ አንተን ላገልግል።