እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ምሳሌ 4:23)

 1. 1. ልባችንን እንጠብቅ፤

  ከኃጢያት እንራቅ፤

  አምላክ የተሰወረውን፣

  ያያል ልባችንን።

  አንዳንዴ ልብ ያታልላል፤

  ሊያስተን ይችላል።

  ለልባችን እንጠንቀቅ፤

  ከመንገድ እንዳንርቅ።

 2. 2. እናዘጋጅ ልባችንን

  ለማወቅ አምላክን።

  ጸሎት፣ ምስጋና፣ ውዳሴ

  እናቅርብ ሁልጊዜ፤

  ይሖዋ የሚነግረንን፣

  መታዘዝ አለብን።

  አምላክን ’ናስደስታለን፤

  ታማኝ ልብ ቢኖረን።

 3. 3. እንመግበው ልባችንን

  እውነት የሆነውን።

  ቃሉ ይንካን፣ ይለውጠን፤

  ያበርታን፣ ኃይል ይስጠን።

  አምላክ ይወዳል ሕዝቦቹን፤

  ይህን እናምናለን።

  በሙሉ ልብ እናምልከው፤

  ወዳጅ እናድርገው።

(በተጨማሪም መዝ. 34:1ን፣ ፊልጵ. 4:8ን እና 1 ጴጥ. 3:4ን ተመልከት።)