በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 33

ሸክማችሁን በይሖዋ ላይ ጣሉ

ኦዲዮ ምረጥ
ሸክማችሁን በይሖዋ ላይ ጣሉ
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(መዝሙር 55)

 1. 1. ይሖዋ ሆይ፣ ተለመነኝ፤

  እባክህ ተመልከተኝ።

  የውስጤን ሥቃይ እይልኝ፤

  አበርታኝ፤ ድፍረት ስጠኝ።

  (አዝማች)

  ሸክምህን ባምላክ ላይ ጣል፤

  ያጸናሃል፤ ይደግፍሃል።

  ጥበቃው አይለይህም፤

  ታማኝ ነው ይረዳሃል።

 2. 2. ምነው የርግብ ክንፍ በኖረኝ፣

  በርሬ ባመለጥኩኝ።

  ሊጎዱኝ ከሚፈልጉ፣

  ከሚጠሉኝ በዳንኩኝ።

  (አዝማች)

  ሸክምህን ባምላክ ላይ ጣል፤

  ያጸናሃል፤ ይደግፍሃል።

  ጥበቃው አይለይህም፤

  ታማኝ ነው ይረዳሃል።

 3. 3. አምላካችን ያጽናናናል፤

  ሰላሙን ይሰጠናል፤

  ብቻችንን አይተወንም፤

  አዛኝ ነው፤ አይጥለንም።

  (አዝማች)

  ሸክምህን ባምላክ ላይ ጣል፤

  ያጸናሃል፤ ይደግፍሃል።

  ጥበቃው አይለይህም፤

  ታማኝ ነው ይረዳሃል።

(በተጨማሪም መዝ. 22:5ን እና 31:1-24ን ተመልከት።)