እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ምሳሌ 14:26)

 1. 1. ይሖዋ ሆይ፣ ተስፋ ሰጠኸን፤

  ከፍ አ’ርገን ’ምናየው።

  ወደር የሌለው ተስፋ ነው፤

  ዓለም ሁሉ ይስማው።

  ሆኖም የሕይወት ውጣ ውረድ

  አንዳንዴ ይከብደናል፤

  የሰጠኸን ብሩህ ተስፋም

  ይጨልምብናል።

  (አዝማች)

  ኃይላችን፣ ተስፋችን፣

  ትምክ’ታችን ነህ።

  ሁሌም ትደግፈናለህ።

  ቃልህን ስንሰብክ

  ልበ ሙሉ ነን፤

  መታመኛችን አንተ ነህ።

 2.  2. አምላክ ሆይ፣ ችግር ሲያጋጥመን

  እንዳንረሳ እርዳን፤

  ከጎናችን እንደምትሆን፣

  እንደምታጽናናን።

  ይህን ስናስብ ደስ ይለናል፤

  ኃይላችን ይታደሳል።

  ስለ ስምህ ለመናገር

  ድፍረት ይኖረናል።

  (አዝማች)

  ኃይላችን፣ ተስፋችን፣

  ትምክ’ታችን ነህ።

  ሁሌም ትደግፈናለህ።

  ቃልህን ስንሰብክ

  ልበ ሙሉ ነን፤

  መታመኛችን አንተ ነህ።

(በተጨማሪም መዝ. 72:13, 14ን፣ ምሳሌ 3:5, 6, 26ን እና ኤር. 17:7ን ተመልከት።)