እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ኢሳይያስ 2:2-4)

 1. 1. እዩ አሻግራችሁ

  እጅግ ከፍ ካለው ጋራ፤

  ዛሬም ይታያል ልቆ

  የአምላክ ተራራ።

  ሕዝቦች ከሩቅ መጡ፤

  ካለም ዳርቻ ሁሉ።

  ‘ኑና ላምላክ ተገዙ’

  እየተባባሉ።

  ቃሉ ተፈጽሟል፤

  ታናሹ ብሔር ታላቅ ሆኗል።

  ይሖዋ ባርኮናል፤

  እድገታችን ይህን ያሳያል።

  ብዙዎች ጎርፈዋል፤

  ከአምላክ ጎን ቆመዋል።

  ታማኝ ይሆናሉ፤

  ለአምላክ ቃል ገብተዋል።

 2.  2. ሄደን እንድንሰብክ

  ጌታ ’የሱስ አዞናል።

  ያምላክ መንግሥት ምሥራች

  ለሁሉም ተዳርሷል።

  ’የሱስ ንጉሥ ሆኗል፤

  ‘ከኔ ጎን ቁሙ’ ይላል።

  ትሑት የሆነ ሁሉ

  ይመራ በቃሉ።

  የእጅግ ብዙ ሕዝብ

  ቁጥር መጨመር ያስደስታል!

  ሁላችን ስላምላክ

  የመመሥከር መብት አግኝተናል።

  ድምፃችን ከፍ ይበል፤

  ሰውን ሁሉ እንጥራ፤

  ጸንቶ ወደሚኖረው

  የአምላክ ተራራ።

(በተጨማሪም መዝ. 43:3፤ 99:9ን፣ ኢሳ. 60:22ን እና ሥራ 16:5ን ተመልከት።)