በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 21

አስቀድማችሁ መንግሥቱን ፈልጉ

ኦዲዮ ምረጥ
አስቀድማችሁ መንግሥቱን ፈልጉ
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ማቴዎስ 6:33)

 1. 1. ይሖዋ የመሠረተው፣

  እሱን የሚያስደስተው፣

  ችግሮችን የሚፈታው፣

  የክርስቶስ መንግሥት ነው።

  (አዝማች)

  በቅድሚያ ፈልግ መንግሥቱን፤

  ምንጊዜም ቢሆን ጽድቁን።

  ክብሩንም ተናገር ለሰው፤

  ታማኝ ሁን፣ አገልግለው።

 2. 2. ለምን ለነገ ’ንጨነቅ?

  ‘እንራብ ይሆን?’ ብለን።

  ባምላክ ይሟላል የቀረው፤

  ካስቀደምን መንግሥቱን።

  (አዝማች)

  በቅድሚያ ፈልግ መንግሥቱን፤

  ምንጊዜም ቢሆን ጽድቁን።

  ክብሩንም ተናገር ለሰው፤

  ታማኝ ሁን፣ አገልግለው።

 3. 3. ምሥራቹን ንገራቸው፤

  ያስተውሉት እርዳቸው።

  ይሖዋንና መንግሥቱን

  እንዲያደርጉ ተስፋቸው።

  (አዝማች)

  በቅድሚያ ፈልግ መንግሥቱን፤

  ምንጊዜም ቢሆን ጽድቁን።

  ክብሩንም ተናገር ለሰው፤

  ታማኝ ሁን፣ አገልግለው።

(በተጨማሪም መዝ. 27:14ን፣ ማቴ. 6:34፤ 10:11, 13ን እና 1 ጴጥ. 1:21ን ተመልከት።)