በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 19

የጌታ ራት

ኦዲዮ ምረጥ
የጌታ ራት
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ማቴዎስ 26:26-30)

 1. 1. ይሖዋ የሰማዩ አባት፣

  የዛሬዋ ቀን ቅዱስ ናት!

  ከዘመናት በፊት ተገለጠ ክብርህ፤

  ፍቅርህ፣ ፍትሕ፣ ጥበብ፣ ኃይልህ።

  አዳንካቸው በፋሲካ ’ለት፤

  ነፃ ወጡ ከባርነት፤

  ከጊዜ በኋላም ጌታችን ሞተልን፤

  የፋሲካው በግ ተሠዋልን።

 2. 2. ፊታችን ያሉት ቂጣና ወይን

  ያስታውሱናል ፍቅርህን።

  ልጅህ ታዛዥ ሆኖ

  ሕይወቱን ሰጥቶናል፤

  የሰው ልጆችን አድኗል።

  ይህን ስጦታ አንረሳውም፤

  አይወጣም ከልባችንም።

  የክርስቶስ ቤዛ

  ሞትን ድል ማድረጉን፣

  እናስባለን ውለታውን።

 3.  3. በፊትህ ቀርበናል በዚህ ቀን፤

  ያንተን ግብዣ ተቀብለን።

  ላሳየኸን ፍቅር

  በመስጠት ልጅህን፣

  አንተን ከልብ ለማመስገን።

  ይህ በዓል አንተን ያስከብራል፤

  በእምነት ያበረታናል።

  እንኑር ሁልጊዜ በክርስቶስ ትም’ርት፤

  ለማግኘት የዘላለም ሕይወት።

(በተጨማሪም ሉቃስ 22:14-20ን እና 1 ቆሮ. 11:23-26ን ተመልከት።)