በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 144

ዓይንህ ሽልማቱ ላይ ያተኩር!

ኦዲዮ ምረጥ
ዓይንህ ሽልማቱ ላይ ያተኩር!
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(2 ቆሮንቶስ 4:18)

 1. 1. ማየት፣ መስማት የተሳናቸው

  ሲፈወሱ ይታይህ ደስታው!

  የሕፃናት ሳቅ ሲያስተጋባ፣

  የትም ሲያብብ ሰላም ደስታ፣

  ሙታን ሲወጡ ከመቃብር፣

  ኃጢያት፣ ዓመፅ ጠፍቶ ከምድር፣

  (አዝማች)

  ተስፋው ላይ ካተኮረ ዓይንህ፣

  በዚህ ጊዜ ትኖራለህ።

 2. 2. ተኩላ ከጠቦት ጋር ይውላል፤

  ጥጃ ከድብ ጋር ይሰማራል።

  ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል፤

  እነሱም ይታዘዙታል።

  ታሪክ ሲሆን እንባና ለቅሶ፣

  ሥቃይ፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት ተረስቶ፣

  (አዝማች)

  ተስፋው ላይ ካተኮረ ዓይንህ፣

  በዚህ ጊዜ ትኖራለህ።

(በተጨማሪም ኢሳ. 11:6-9፤ 35:5-7ን እና ዮሐ. 11:24ን ተመልከት።)