እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ማቴዎስ 11:28-30)

 1. 1. ጌታችን ኢየሱስ ሲኖር በምድር፤

  ኩራት የሌለበት ትሑት ሰው ነበር።

  ባምላክ ዓላማ ውስጥ ልዩ ቦታ ’ለው፤

  ያም ሆኖ ምንጊዜም ልቡ ትሑት ነው።

 2. 2. ቀርቧል ግብዣው ሸክም ለከበዳችሁ፤

  ፈቃደኛ ነው ሸክሙን ሊጋራችሁ።

  መንግሥቱን ማስቀደም እረፍት ያስገኛል፤

  ጌታችን ገር ነው፤ ትሑት ሰው ይወዳል።

 3. 3. “ወንድማማች ናችሁ” ብሎናል ጌታ፤

  መሪያችን አንድ ነው ለሱ ’ንገዛ።

  ገሮች ባምላካችን ፊት ዋጋ ’ላቸው፤

  አምላክ ቃል ገብቷል ምድርን ሊያወርሳቸው።

(በተጨማሪም ምሳሌ 3:34ን፣ ማቴ. 5:5፤ 23:8ን እና ሮም 12:16ን ተመልከት።)