በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 117

ጥሩነት

ኦዲዮ ምረጥ
ጥሩነት
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(2 ዜና መዋዕል 6:41)

 1. 1. ይሖዋ ሆይ፣ ደግ አምላክ ነህ።

  ብዙ ነው በረከትህ።

  ወደር የለው ጥሩነትህ፤

  ታማኝ አምላካችን ነህ።

  ይገባናል ለማንለው

  ሞገስህ ’ናመስግንህ።

  አምልኳችን ይገባሃል፤

  በደስታ ’ናገልግልህ።

 2. 2. የሕዝቦችህ መልካም ምግባር፣

  ወንጌሉን መስበካቸው፣

  ያሳያል ጥሩነትህን

  እንደሆንክ አምላካቸው።

  በደግነት አስተማርከን፤

  እረኞችን ሾምክልን።

  መንፈስህን ’ባክህ ስጠን፤

  እኛም ጥሩ እንድንሆን።

 3. 3. ሳናዳላ ለሁሉም ሰው

  ስናሳይ ጥሩነትን፣

  ወንድሞችን ስንረዳቸው

  ስጠን በረከትህን።

  በቤተሰብ፣ በጉባኤ፣

  ባገልግሎት ላይ ስንሆን

  በመንፈስህ በመታገዝ

  እናሳይ ጥሩነትን።

(በተጨማሪም መዝ. 103:10ን፣ ማር. 10:18ን፣ ገላ. 5:22ን እና ኤፌ. 5:9ን ተመልከት።)