እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ነህምያ 8:10)

 1. 1. ጊዜው ያበስራል መንግሥቱ መቅረቡን፤

  ይገባናል ማወጅ ይህን።

  መዳናችን ቀርቧል እዩ ወደ ላይ፤

  እፎይ ልንል ነው ከሥቃይ!

  (አዝማች)

  የአምላክ ደስታ ምሽጋችን ነው።

  በግለት እናወድሰው።

  ተስፋው ያስፈንድቀን፣ እናመስግነው፤

  ለአምላክ ይዘምር ሁሉም ሰው።

  የአምላክ ደስታ ምሽጋችን ነው።

  ስሙን ሁሉም ሰው ይወቀው።

  ለንጉሣችን ታማኞች በመሆን፣

  በደስታ ’ናገለግላለን።

 2. 2. ያምላክ ባሮች ወደ’ሱ ተመልከቱ፤

  እሱ ብርቱ ነው አትፍሩ።

  እንነሳ ’ናወድሰው በግለት፤

  በደስታ እንዘምርለት!

  (አዝማች)

  የአምላክ ደስታ ምሽጋችን ነው።

  በግለት እናወድሰው።

  ተስፋው ያስፈንድቀን፣ እናመስግነው፤

  ለአምላክ ይዘምር ሁሉም ሰው።

  የአምላክ ደስታ ምሽጋችን ነው።

  ስሙን ሁሉም ሰው ይወቀው።

  ለንጉሣችን ታማኞች በመሆን፣

  በደስታ ’ናገለግላለን።

(በተጨማሪም 1 ዜና 16:27ን፣ መዝ. 112:4ን፣ ሉቃስ 21:28ን እና ዮሐ. 8:32ን ተመልከት።)