እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(መዝሙር 19)

 1. 1. ይሖዋ ሆይ፣ ድንቅ ነው ፍጥረትህ፤

  ያውጃሉ ሰማያት ክብርህን።

  ቃል ባይኖርም፣ ድምፃቸው ባይወጣም፣

  መል’ክታቸው አስተጋባ ባለም።

  ቃል ባይኖርም፣ ድምፃቸው ባይወጣም፣

  መል’ክታቸው አስተጋባ ባለም።

 2. 2. ጥበብ አለው አንተን ’ሚፈራ ሰው፤

  ንግግሩ፣ ድርጊቱ ንጹሕ ነው።

  ት’ዛዛትህ ከወርቅ ይበልጣሉ፤

  ለትሑታን ጥበብ ይሰጣሉ።

  ት’ዛዛትህ ከወርቅ ይበልጣሉ፤

  ለትሑታን ጥበብ ይሰጣሉ።

 3. 3. ትርጉም ያለው ሕይወት የምንመራው

  መመሪያህን ስለምንጠብቅ ነው።

  ለሚያከብሩ ታላቁን ስምህን

  ታሳያቸዋለህ ሞገስህን።

  ለሚያከብሩ ታላቁን ስምህን

  ታሳያቸዋለህ ሞገስህን።

(በተጨማሪም መዝ. 12:6፤ 89:7፤ 144:3ን እና ሮም 1:20ን ተመልከት።)