በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 105

“አምላክ ፍቅር ነው”

ኦዲዮ ምረጥ
“አምላክ ፍቅር ነው”
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(1 ዮሐንስ 4:7, 8)

 1. 1. ይሖዋ አምላክ ፍቅር ነው፤

  ጋብዞናል እንድንመስለው።

  ላምላክ፣ ለሰው ፍቅር ካለን፣

  ጥሩ ሰው እንሆናለን።

  ሕይወት ትርጉም የሚኖረው፣

  ፍቅር ካለን ብቻ ነው።

  የክርስቶስ ዓይነት ፍቅር፣

  እንዳለን እናስመሥክር።

 2. 2. ላምላክ፣ ለ’ውነት ያለን ፍቅር፣

  ያነሳሳል ለተግባር።

  ይሖዋ ሊረዳን ይሻል፤

  ስንወድቅ ያነሳናል።

  ፍቅር አይቀናም፤ ንጹሕ ነው፤

  ይታገሳል፤ ደግ ነው።

  ይጨምር፣ ይደግ ፍቅራችን፤

  በረከት እናጭዳለን።

 3. 3. ቂም መያዝ አይጠቅምም ይቅር፤

  በደልንም አትቁጠር።

  ይሖዋን መስማት ይበጃል፤

  መንገዱን ያሳይሃል።

  አምላክን፣ ሰውን እንውደድ፤

  ይህ ነው የጌታ ፈቃድ።

  የይሖዋ ዓይነት ፍቅር፣

  ለማሳየት እንጣር።

(በተጨማሪም ማር. 12:30, 31ን፣ 1 ቆሮ. 12:31–13:8ን እና 1 ዮሐ. 3:23ን ተመልከት።)