በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 100

እንግዳ ተቀባይ ሁኑ

ኦዲዮ ምረጥ
እንግዳ ተቀባይ ሁኑ
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(የሐዋርያት ሥራ 17:7)

 1. 1. እንግዳ ተቀባይ ነው ይሖዋ ’ባት፤

  ለሁሉም ያስባል፣ ማዳላት አያውቅ።

  ዝናብና ፀሐይ

  ለሁሉም ይሰጣል፤

  መልካም ስጦታው ያረካናል።

  ለተቸገረ ሰው ጥሩ ስንሆን፣

  ይሖዋ አምላክን እንመስለዋለን።

  ለሌሎች ልባዊ

  ደግነት ካሳየን፣

  ካምላክ ወሮታ ’ናገኛለን።

 2. 2. የተቸገሩትን ስንደግፋቸው፣

  መልካም ውጤት አለው ስናዝንላቸው።

  ባናውቃቸው እንኳ

  እንቀበላቸው፤

  በችግር ጊዜ እንርዳቸው።

  ልክ እንደ ሊዲያ ‘ቤቴ ኑ’ እንበል፤

  ቤታችን ’ሚመጣ ሰው እፎይ ይበል።

  ይሖዋ እንደ’ሱ

  ደጎች የሆኑትን፣

  ምንጊዜም ይባርካቸዋል።

(በተጨማሪም ሥራ 16:14, 15ን፣ ሮም 12:13ን፣ 1 ጢሞ. 3:2ን፣ ዕብ. 13:2ን እና 1 ጴጥ. 4:9ን ተመልከት።)