በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 3 2017 | የአራቱ ፈረሰኞች ግልቢያ—በሕይወትህ ላይ ለውጥ ያመጣል?

ምን ይመስልሃል?

በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘውን ስለ አራቱ ፈረሰኞች የሚናገረውን ትንቢት ብዙዎች ያውቁታል። ይህ ትንቢት አንዳንዶችን ያስፈራቸዋል። ሌሎች ደግሞ ስለዚህ ትንቢት ይበልጥ ለማወቅ ይጓጓሉ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ስላሉ ትንቢቶች ምን እንደሚል ተመልከት፦

“የዚህን ትንቢት ቃል ጮክ ብሎ የሚያነብ ደስተኛ ነው፤ እንዲሁም ቃሉን የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፉትን ነገሮች የሚጠብቁት ደስተኞች ናቸው።”ራእይ 1:3

ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም የአራቱ ፈረሰኞች ግልቢያ ለእኛ ምሥራች ሊሆን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

 

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ስለ አራቱ ፈረሰኞች የሚገልጸው ራእይ

ነጭ፣ ቀይ፣ ጥቁር እና ግራጫ ቀለም ያላቸው አራት ፈረሶች። የአራቱ ፈረሰኞች ግልቢያ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ከተጠቀሱት በብዙዎች ዘንድ የሚታወቁ ዘገባዎች መካከል አንዱ ነው።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

አራቱ ፈረሰኞች—እነማን ናቸው?

በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘውን የዚህን ራእይ ትርጉም ለመረዳት ሞክር።

ተጨማሪ ማስረጃ

ታተናይ ማን እንደሆነ አታውቅ ይሆናል፤ ይሁንና ስለ እሱ የሚገልጹ አርኪኦሎጂያዊ ግኝቶች የሚያረጋግጡት ነገር አለ።

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል

ከምንም ነገር በላይ የሚያስደስተኝ ቤዝቦል መጫወት ነበር!

ሳሙኤል ሃሚልተን ከምንም በላይ የሚያስደስታቸው ቤዝቦል መጫወት ነበር፤ ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናታቸው ሕይወታቸው እንዲለወጥ አድርጓል።

በእምነታቸው ምሰሏቸው

“አንቺ በጣም ውብ ሴት ነሽ”

በግብፅ የነበሩት የፈርዖን መኳንንት ሣራ በጣም ውብ እንደሆነች ተመለከቱ። ከዚያ በኋላ የሆነው ነገር ያስገርምህ ይሆናል።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

አምላክ አንዱን ዘር ከሌላው ከፍ አድርጎ ይመለከታል? አንዳንዶች አምላክ የተወሰኑ ዘሮችን እንደባረከ ሌሎቹን ደግሞ እንደረገመ ይሰማቸዋል።

በተጨማሪም . . .

የራእይ መጽሐፍ የያዘው መልእክት ምንድን ነው?

ይህ መጽሐፍ ራሱ እንደሚገልጸው በውስጡ ያለውን መልእክት የሚያነብቡና ተረድተው ሥራ ላይ የሚያውሉ ሰዎች ደስተኞች ይሆናሉ።