ምን ይመስልሃል?

አሁን ካለንበት የሥልጣኔ ዘመን አንጻር መጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ ያለፈበት ይመስልሃል? ወይስ ምክሩ እኛ ላለንበት ዘመንም ይሠራል? መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እንዲህ ይላል፦ “ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው፤ እንዲሁም ለማስተማር . . . ይጠቅማሉ።”2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17

ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን አንዳንድ ጥበብ ያዘሉ ምክሮች ይዟል፤ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ይበልጥ አስደሳች እንዲሆንልህ ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።