በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ  |  ኅዳር 2015

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የሞቱ ሰዎች ዳግመኛ በሕይወት ይኖራሉ?

የሕይወት ፈጣሪ መልሶ ሕይወትን መስጠት ይችላል

የሕይወት ምንጭ ይሖዋ አምላክ ነው። (መዝሙር 36:9) ታዲያ ፈጣሪ የሞቱ ሰዎች ዳግመኛ በሕይወት እንዲኖሩ ማድረግ ያቅተዋል? አምላክ ወደፊት ይህን እንደሚፈጽም መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (የሐዋርያት ሥራ 24:15ን አንብብ።) ሆኖም አምላክ እንዲህ የሚያደርገው ለምንድን ነው?

ፈጣሪያችን ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም እንዲኖሩ ዓላማው ነው። (ዘፍጥረት 1:31፤ 2:15-17) አሁንም ቢሆን ሰዎች ለዘላለም እንዲኖሩ ይፈልጋል። በአሁኑ ጊዜ ሕይወታችን በመከራ የተሞላና በአጭሩ የሚቀጭ በመሆኑ በጣም ያዝናል።—ኢዮብ 14:1, 14, 15ን አንብብ።

ከሞት የሚነሱ ሰዎች የሚኖሩት የት ነው?

አምላክ ሰውን የፈጠረው በሰማይ እንዲኖር ነው? በፍጹም። አምላክ በሰማይ እንዲኖሩ የፈጠረው መላእክትን ነው። ሰዎችን የፈጠረው በምድር ላይ እንዲኖሩ ነው። (ዘፍጥረት 1:28፤ ኢዮብ 38:4, 7) ይህንን በአእምሮህ በመያዝ እስቲ ኢየሱስ ከሞት ስላስነሳቸው ሰዎች አስብ። ከሞት ያስነሳቸው ሰዎች የኖሩት እዚሁ ምድር ላይ ነው። ወደፊትም ቢሆን ትንሣኤ የሚያገኙ አብዛኞቹ ሰዎች የሚኖሩት በምድር ላይ ነው።—ዮሐንስ 5:28, 29ን እና 11:44ን አንብብ።

ሆኖም አምላክ እሱ የመረጣቸው የተወሰነ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በሰማይ መኖር እንዲችሉ መንፈሳዊ አካል ይዘው ከሞት እንዲነሱ ያደርጋል። (ሉቃስ 12:32፤ 1 ቆሮንቶስ 15:49, 50) በሰማይ ለመኖር ትንሣኤ የሚያገኙ ሰዎች ከክርስቶስ ጋር ነገሥታት ሆነው ምድርን ይገዛሉ።—ራእይ 5:9, 10ን አንብብ።