በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ  |  ሚያዝያ 2015

 የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | መጽሐፍ ቅዱስን መማር ትፈልጋለህ?

መጽሐፍ ቅዱስን መማር ለምን አስፈለገ?

መጽሐፍ ቅዱስን መማር ለምን አስፈለገ?
  • የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?

  • መከራ የሚደርስብንና የምንሞተው ለምንድን ነው?

  • የወደፊቱ ጊዜ ምን ይዞ ይመጣል?

  • አምላክ ያስብልኛል?

እንዲህ ስላሉ ጥያቄዎች አስበህ ታውቃለህ? ከሆነ አንተ ብቻ ሳትሆን በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎችም ስለ እነዚህ አስፈላጊ ጥያቄዎች ያስባሉ። ታዲያ ለጥያቄዎቹ መልስ ማግኘት ይቻላል?

በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች፣ መልስ ማግኘት እንደሚቻል ይናገራሉ። እንዲህ የሚሉት ለምንድን ነው? ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለጥያቄዎቻቸው አጥጋቢ መልስ ስላገኙ ነው። አንተስ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ ማወቅ ትፈልጋለህ? ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች * ባዘጋጁት ነፃ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ፕሮግራም መጠቀም ትችላለህ።

በእርግጥ፣ መጽሐፍ ቅዱስን የመማር ጉዳይ ሲነሳ አንዳንድ ሰዎች እንደሚከተለው ያሉ ሐሳቦችን ሲሰነዝሩ ይሰማል፦ “ጊዜ የለኝም።” “መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት በጣም ከባድ ነው።” “አንድ ዓይነት ግዴታ ውስጥ መግባት አልፈልግም።” ይሁን እንጂ ሌሎች ከዚህ የተለየ አመለካከት አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስን እንዲማሩ የቀረበላቸውን ግብዣ በደስታ ተቀብለዋል። ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሱትን ሰዎች እንደ ምሳሌ እንውሰድ።

  • “ወደ ካቶሊክና ፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት፣ ወደ ሲክ ቤተ መቅደስ እንዲሁም ወደ ቡዲስት ገዳም ሄጃለሁ፤ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሥነ መለኮት ትምህርት ተምሬአለሁ። ሆኖም ስለ አምላክ ከነበሩኝ ጥያቄዎች ለአብዛኞቹ መልስ ማግኘት አልቻልኩም። ከዚያም አንዲት የይሖዋ ምሥክር ወደ ቤቴ መጣች። ለጥያቄዎቼ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሰጠችኝ መልስ ስለተደነቅሁ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ተስማማሁ።”—ጊልእንግሊዝ

  • “ስለ ሕይወት ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ፤ ይሁን እንጂ የቤተ ክርስቲያኔ ፓስተር የሰጠኝ መልስ አላረካኝም። ነገር ግን አንድ የይሖዋ ምሥክር መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመጠቀም ጥያቄዎቼን መለሰልኝ። ተጨማሪ ነገር መማር እፈልግ እንደሆነ ሲጠይቀኝ ግብዣውን በደስታ ተቀበልኩ።”—ኮፊቤኒን

  • “የሞቱ ሰዎች ስለሚገኙበት ሁኔታ ለማወቅ እጓጓ ነበር። ሙታን በሕይወት ያሉትን ሰዎች ሊጎዱ ይችላሉ ብዬ ባምንም ስለ ጉዳዩ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ለማወቅ ፈለግሁ። ስለዚህ የይሖዋ ምሥክር ከሆነ አንድ ጓደኛዬ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀመርኩ።”—ዡዜብራዚል

  • “መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ብሞክርም ሊገባኝ አልቻለም። ከዚያም የይሖዋ ምሥክሮች ወደ ቤቴ መጡና ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን በግልጽ አብራሩልኝ። የይሖዋ ምሥክሮች ተጨማሪ ነገር ያስተምሩኝ እንደሆነ ለማየት ፈለግሁ።”—ዴኒዝሜክሲኮ

  • “‘አምላክ ያስብልኛል?’ የሚለው ጉዳይ ያሳስበኝ ነበር። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ላስጻፈው አምላክ ጸለይኩ። በማግሥቱ የይሖዋ ምሥክሮች ወደ ቤቴ መጡ፤ ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስን እንድማር ያቀረቡልኝን ግብዣ ተቀበልኩ።”—አንጁኔፓል

እነዚህ አስተያየቶች “መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ ደስተኞች ናቸው” የሚሉትን የኢየሱስ ቃላት ያስታውሱናል። (ማቴዎስ 5:3) አዎ፣ የሰው ልጆች በተፈጥሯቸው ስለ አምላክ የማወቅ ፍላጎት አላቸው። ይህን ፍላጎታቸውን ማርካት የሚችለው አምላክ ብቻ ሲሆን ይህን የሚያደርገውም በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ነው።

ታዲያ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚሰጥበት ፕሮግራም ምን ይመስላል? መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ሊጠቅምህ የሚችለው እንዴት ነው? የእነዚህ ጥያቄዎች መልስ በሚቀጥለው ርዕስ ላይ ይብራራል።

^ አን.8 መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአምላክ ስም ይሖዋ ነው።