በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ  |  ሚያዝያ 2014

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ኢየሱስ ወደፊት ምን ያደርጋል?

ኢየሱስ በ33 ዓ.ም. ሞቶ ከተነሳ በኋላ ወደ ሰማይ አርጓል። ይህ ከሆነ ከብዙ ጊዜ በኋላ ደግሞ ኢየሱስ ንጉሥ እንዲሆን ሥልጣን ተሰጥቶታል። (ዳንኤል 7:13, 14) ወደፊት ኢየሱስ ይህን ንጉሣዊ ሥልጣኑን ተጠቅሞ ሰላምን በዓለም በሙሉ ያሰፍናል፤ እንዲሁም ድህነትን ያስወግዳል።መዝሙር 72:7, 8, 13ን አንብብ።

ኢየሱስ ንጉሥ እንደመሆኑ መጠን ክፋትን ከምድር ላይ ጠራርጎ ያስወግዳል

ኢየሱስ የሰው ልጆችን በሚያስተዳድርበት ወቅት በርካታ አስደናቂ ነገሮችን ያከናውናል። አባቱ የሰጠውን ኃይል ተጠቅሞ የሰው ልጆች ፍጹማን እንዲሆኑ ያደርጋል። በዚያን ጊዜ እርጅናና ሞት ከምድር ላይ ስለሚወገዱ የሰው ልጆች ደስታ የተሞላበት ሕይወት ያጣጥማሉ።ዮሐንስ 5:26-29ን እና 1 ቆሮንቶስ 15:25, 26ን አንብብ።

ኢየሱስ በአሁኑ ጊዜ ምን እያደረገ ነው?

በአሁኑ ጊዜ ኢየሱስ፣ እውነተኛ ተከታዮቹ በዓለም ዙሪያ የሚያከናውኑትን የስብከት ሥራ በበላይነት እየመራ ነው። የኢየሱስ ተከታዮች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ መንግሥት ምን እንደሚል ለሰዎች ያስተምራሉ። የአምላክ መንግሥት ሰብዓዊ መንግሥታትን በሙሉ እስከሚያጠፋበት ጊዜ ድረስ ተከታዮቹ የሚያከናውኑትን ሥራ መደገፉን እንደሚቀጥል ኢየሱስ ተናግሯል።ማቴዎስ 24:14ን እና ማቴዎስ 28:19, 20ን አንብብ።

ኢየሱስ፣ እውነተኛውን የክርስቲያን ጉባኤ በመጠቀም ሰዎች የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ እያደረገ ነው። እንዲሁም እነዚህ ሰዎች በዚህ ክፉ ሥርዓት ላይ ከሚደርሰው ጥፋት ተርፈው አምላክ ቃል ወደገባው አዲስ ዓለም እንዲገቡ ያደርጋቸዋል።2 ጴጥሮስ 3:7, 13ን እና ራእይ 7:17ን አንብብ።