በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ  |  ታኅሣሥ 2012

የተሻለ ነገር አግኝተዋል

የተሻለ ነገር አግኝተዋል

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ገናን ላለማክበር መርጠዋል። ታዲያ እንዲህ ያለ ውሳኔ በማድረጋቸው ምን ይሰማቸዋል? የቀረባቸው ነገር እንዳለ በማሰብ ይቆጫሉ? ልጆቻቸውስ የተነፈጉት ነገር እንዳለ ይሰማቸዋል? በመላው ዓለም የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚሉ እስቲ እንመልከት።

ኢቭ

ኢየሱስ ክርስቶስን ማስታወስ፦ “የይሖዋ ምሥክር ከመሆኔ በፊት ወደ ቤተ ክርስቲያን የምሄደው ከስንት አንዴ ነበር። የምሄደውም ለገና ወይም ለፋሲካ በዓል ብቻ ነበር። ሆኖም በዚያ ጊዜም እንኳ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አላስብም። አሁን ገናን ማክበር አቁሜያለሁ፤ ይሁን እንጂ በሳምንት ሁለት ጊዜ በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ የምገኝ ከመሆኑም በላይ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን ነገር ለሌሎች አስተምራለሁ!”—ኢቭ፣ አውስትራሊያ

ሩቤን

በመስጠት የሚገኘው ደስታ፦ “ሰዎች ባልጠበቅሁት ጊዜ ስጦታ ሲሰጡኝ በጣም እደሰታለሁ። ሳላስበው አንድ ነገር ሲደረግልኝ ደስ ይለኛል! በተጨማሪም ካርድ አዘጋጅቼና ሥዕል ስዬ ለሌሎች መስጠት እወዳለሁ፤ ምክንያቱም እንዲህ ሳደርግ እኔም ሆንኩ እነሱ እንደሰታለን።”—ሩቤን፣ ሰሜን አየርላንድ

ኤምሊ

ችግረኞችን መርዳት፦ “ለታመሙ ሰዎች ምግብ ማዘጋጀት እንወዳለን። እነሱን ለማስደሰት ስንል አንዳንድ ጊዜ አበባ፣ ኬክ ወይም አነስተኛ ስጦታ ይዘን በመሄድ እንጠይቃቸዋለን። እነዚህን ሰዎች በዓመቱ ውስጥ በየትኛውም ጊዜ መጠየቅ ስለምንችል ይህን ማድረግ ያስደስተናል።”—ኤምሊ፣ አውስትራሊያ

ዌንዲ

ከቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፦ “ቤተሰባችን አንድ ላይ ተሰባስቦ ዘና በሚልበት ጊዜ ልጆቻችን ከአጎቶቻቸው፣ ከአክስቶቻቸው፣ ከአያቶቻቸው እንዲሁም ከአጎቶቻቸውና ከአክስቶቻቸው ልጆች ጋር ለመተዋወቅ አጋጣሚ ያገኛሉ። ይህን የምናደርገው በዓል ጠብቀን ስላልሆነ ጫና አይፈጥርብንም፤ የቤተሰባችን አባላትም የምንጠይቃቸው ስለምንወዳቸው እንደሆነ ያውቃሉ።”—ዌንዲ፣ ኬይማን ደሴቶች

ሳንድራ

ሰላም፦ “በገና ጊዜ ብዙ ሰዎች በሥራ በጣም ስለሚወጠሩ ስለ ሰላም ለማሰብ ጊዜ አይኖራቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ ለሰው ልጆች የሚሰጠውን ተስፋ ስለተማርኩ አሁን አልጨነቅም። ልጆቼ ወደፊት አስደሳች ሕይወት እንደሚጠብቃቸው ተምሬያለሁ።”—ሳንድራ፣ ስፔን