በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

“አምላክ ለሚወዳቸው ሰዎች ሰላም ይሁን”

“አምላክ ለሚወዳቸው ሰዎች ሰላም ይሁን”

“በሰማያት ለአምላክ ክብር ይሁን፤ በምድርም አምላክ ለሚወዳቸው ሰዎች ሰላም ይሁን።”—ሉቃስ 2:14

አንዳንዶች ገናን የሚያከብሩበት ምክንያት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱና ሌሎች የሃይማኖት መሪዎች በየዓመቱ የሰላምን መልእክት የሚሰብኩ ሲሆን መላእክቱ “በምድርም አምላክ ለሚወዳቸው ሰዎች ሰላም ይሁን” በማለት የተናገሩት ነገር በገና ሰሞን እንደሚፈጸም ተስፋ ያደርጋሉ። ሌሎች ደግሞ ገናን ለማክበር ልዩ መንፈሳዊ ጉዞ ያደርጋሉ።

ይህን ማድረግ ተፈታታኝ የሆነው ለምንድን ነው?

በገና ሰሞን የሚታየው ሰላማዊ ሁኔታ ጊዜያዊ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ አውሮፓ በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ትታመስ በነበረችበት በታኅሣሥ 1914 የብሪታንያና የጀርመን ወታደሮች ከየምሽጎቻቸው ወጥተው ገናን አንድ ላይ አክብረዋል። ወታደሮቹ የነበራቸውን ምግብና መጠጥ እንዲሁም ሲጋራ ተካፍለዋል። ከዚያም አልፎ አብረው እግር ኳስ ተጫውተው ነበር። ይሁን እንጂ የተኩስ አቁም ስምምነቱ አልዘለቀም። አንድ የብሪታንያ ወታደር ከጦር ግንባሩ በላከው ደብዳቤ ላይ አንድ የጀርመን ወታደር እንዲህ እንዳለው ገልጾ ነበር፦ “ዛሬ ሰላም አለን። ነገ ግን አንተም ለአገርህ እኔም ለአገሬ እንዋጋለን።”

ሊረዱን የሚችሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች

“ሕፃን ተወልዶልናልና፤ . . . ስሙም፣ . . . የሰላም ልዑል ይባላል። ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም።” (ኢሳይያስ 9:6, 7) ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረው ይህ ትንቢት የሚያጽናና አይደለም? ይሁን እንጂ ኢየሱስ እዚህ ምድር ላይ የተወለደው በዓመት አንድ ቀን ሰላም ለማምጣት አይደለም። በሰማይ ሆኖ ምድርን ሲያስተዳድር ፍጻሜ የሌለው እውነተኛ ሰላም ያመጣል።

“በእኔ አማካኝነት ሰላም [ይኑራችሁ።] በዓለም ሳላችሁ መከራ ይደርስባችኋል፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።” (ዮሐንስ 16:33) በዛሬው ጊዜም እንኳ ኢየሱስ በተከታዮቹ መካከል ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋል። እውነት ነው፣ ክርስቲያኖች መከራ አለባቸው። ሆኖም ለመጽሐፍ ቅዱስ ምስጋና ይግባውና፣ መከራ የኖረበትን ምክንያት እንዲሁም ኢየሱስ ዘላቂ ሰላም የሚያመጣበትን መንገድ ያውቃሉ። ስለዚህ የአእምሮ ሰላም አላቸው።

የይሖዋ ምሥክሮች ዜግነታቸው፣ የቆዳ ቀለማቸው፣ ብሔራቸው አሊያም ቋንቋቸው ምንም ሆነ ምን የኢየሱስን ትምህርት ተግባራዊ ስለሚያደርጉ ሰላም አግኝተዋል። በመንግሥት አዳራሻቸው በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ በመገኘት ይህን ለምን ራስህ አታረጋግጥም? አንተም እንደ ሌሎች ብዙ ሰዎች በይሖዋ ምሥክሮች መካከል የሚታየው ሰላም በገና በዓል ወቅት ይኖራል ተብሎ ከሚታሰበው ሰላማዊ ሁኔታ የላቀ እንደሆነ መገንዘብህ አይቀርም።

የይሖዋ ምሥክሮች የቆዳ ቀለማቸው ወይም ቋንቋቸው ምንም ይሁን ምን ሰላምና አንድነት አላቸው። በመንግሥት አዳራሻቸው በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ በመገኘት ይህን ለምን ራስህ አታረጋግጥም?