“አቤት ዝናቡ!” አለች

ሚጣ እያለቀሰች።

“መቼ ነው የሚያቆመው?”

ብላም አሰበች።

በድንገት ግን

ፀሐይዋ ብቅ አለች!

ዝናቡ አቆመ፣

ሚጣም ተደሰተች!

በደስታ እየቦረቀች

ወደ ደጅ ስትወጣም፣

አንድ ነገር አየች

በጣም የሚያስገርም!

እየተደነቀች ሚጣ እንዲህ አለች፦

“ለካስ አበባ የሚበቅለው

አምላክ ዝናብ ሲያዘንብ ነው!”

ለወላጆች የተሰጠ መመሪያ

ልጃችሁ ከሥዕሉ ላይ የሚከተሉትን ማግኘት ይችላል?

  • መስኮት
  • ሚጣ
  • አበቦች
  • ወፍ
  • ዛፍ

ልጃችሁ የተደበቁትን ነገሮች ማግኘት ይችላል?

  • ጥንዚዛ
  • አውሮፕላን

የሐዋርያት ሥራ 14:17ን አንብቡ። ይሖዋ ዝናብን የፈጠረው ለምንድን ነው?