በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 2012 | ሙስና—ምን ያህል ተስፋፍቷል?

የሙስና መንስኤዎች ምንድን ናቸው? እነዚህ ተከታታይ ርዕሶች መንስኤዎቹንና መፍትሔውን ይጠቁማሉ።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ሙስና ምን ያህል ተስፋፍቷል?

ሙስና የሚያስከትለው ችግር በዓለም ዙሪያ የሚታይና ማንኛውንም ሰው የሚነካ ነው፤ እንዲያውም አንዳንዴ የሚያስከትለው መዘዝ ከፍተኛ ነው።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ሙስናን ማጥፋት ያልተቻለው ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ላይ ከባድ መከራና ሥቃይ እንዲኖር ያደረጉት ሦስት ጎጂ ተጽዕኖዎች የትኞቹ እንደሆኑ ይናገራል።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ሙስና በተስፋፋበት ዓለም ውስጥ ሐቀኛ መሆን ይቻላል?

ይህ ርዕስ ሁለት ሰዎች ሐቀኛ መሆንና የሥነ ምግባር መመሪያዎችን መጠበቅ የሚያስገኘውን ጥቅም የተገነዘቡት እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ሙስና ይወገዳል!

አምላክ ምድራችንን ከሙስና ለማጽዳት በቅርቡ እርምጃ ይወስዳል። ይህን የሚያደርገው እንዴት ነው?

የሕይወት ታሪክ

የአምላክ ቃል ያለው ኃይል የሂንዱ እምነት በሚከተል ቤተሰብ ውስጥ

የሂንዱ እምነት ተከታይ የሆነ አንድ ቤተሰብ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ ደስተኛ ሕይወት እንዲመራ ያስቻለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውይይት

አምላክ ሰዎችን በገሃነመ እሳት ያቃጥላል?

አምላክ ክፉ ሰዎችን በሚቀጣበት ጊዜም እንኳ ፍርዱ ፍትሐዊ ነው ብለን እንድናምን የሚያደርገን በቂ ምክንያት አለን።

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ኢየሩሳሌም በ70 ዓ.ም. ከመጥፋቷ በፊት ክርስቲያኖች ከይሁዳ ሸሽተው እንደወጡ የሚያሳይ ማስረጃ አለ? ለመሆኑ ‘የነቢያት ልጆች’ የተባሉት እነማን ናቸው?

ከአምላክ ቃል ተማር

ለዘላለም መኖር ይቻላል?

የሕይወት ምንጭ የሆነው ይሖዋ አምላክ ሰዎች ለዘላለም እንዲኖሩ ማድረግ የሚችል ከመሆኑም በላይ ይህንን ለማድረግም ቃል ገብቷል።

ወደ አምላክ ቅረብ

“በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ”

በዘመናት የሸመገለው የተባለው ማን ነው? የዳንኤል ራእይ ምን ትርጉም አለው?

በእምነታቸው ምሰሏቸው

“ምግባረ መልካም ሴት”

ሞዓባዊቷ ሩት እስራኤል ውስጥ የምትኖር የባዕድ አገር ሴት ናት። ለመሆኑ ሩትን “ምግባረ መልካም ሴት” እንድትባል ያደረጋት ምንድን ነው?

አንባቢያን የሚያነሱት ጥያቄ

አንድ ሰው ደስተኛ ለመሆን የግድ ማግባት ይኖርበታል?

ትዳር የሌላቸው ክርስቲያኖች ደስተኛ ሊሆኑ ይችላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች ትዳርን በሚመለከት ምን አመለካከት ሊኖራቸው እንደሚገባ እንዲሁም ነጠላነትን አስመልክቶ ማን ፍጹም ምሳሌያችን ሊሆን እንደሚችል ይናገራል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል

ይህ ርዕስ የሁለት ሰዎችን ታሪክ ይዟል፤ እነዚህ ሰዎች የአልኮል መጠጥና የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነትን ጨምሮ መጥፎ ልማዶቻቸውን እርግፍ አድርገው በመተው ደስተኛ ሕይወት መምራት የጀመሩት እንዴት ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መልመጃዎች

ትልቅ ቦታ የማግኘት ምኞት እንዳያድርብህ ተጠንቀቅ!

የንጉሥ ዳዊት ልጅ የሆነው አቤሴሎም የአባቱን ዙፋን ለመንጠቅ ሞክሮ ነበር፤ ይሁንና ይህ ምኞቱ ከፍተኛ ኪሳራ አስከትሎበታል።