በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም  |  መስከረም 2014

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ዳዊት በመዝሙር 37:25 ላይ የተናገረውና ኢየሱስ በማቴዎስ 6:33 ላይ የገለጸው ሐሳብ ይሖዋ አንድ ክርስቲያን እንዲራብ ፈጽሞ እንደማይፈቅድ የሚያሳዩ ናቸው?

ዳዊት “ዳድቅ ሲጣል፣ ዘሩም እንጀራ ሲለምን አላየሁም” ሲል ጽፏል። ይህን ሐሳብ የገለጸው ከራሱ ተሞክሮ በመነሳት ነው። ዳዊት አምላክ ሕዝቦቹን ምንጊዜም እንደሚንከባከብ አሳምሮ ያውቅ ነበር። (መዝ. 37:25) ይሁን እንጂ ዳዊት የተናገረው ሐሳብ የይሖዋ አምላኪዎች የሚያስፈልጋቸውን ነገር በፍጹም እንደማያጡ የሚያመለክት አይደለም።

ዳዊት ራሱ በጣም የተቸገረበት ጊዜ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ ከሳኦል በሸሸበት ወቅት እንዲህ ያለ ሁኔታ አጋጥሞት ነበር። ዳዊት በቂ ስንቅ ስላልነበረው ለራሱና ከእሱ ጋር ለነበሩት ሰዎች የሚሆን እንጀራ ለማግኘት ጠይቋል። (1 ሳሙ. 21:1-6) በመሆኑም በዚህ ጊዜ ዳዊት ‘እንጀራ ለምኗል።’ ሆኖም በዚያ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይሖዋ እንዳልተወው ያውቅ ነበር። እንደ እውነቱ ከሆነ ዳዊት ለማኝ እንደነበረ የሚገልጽ ታሪክ ፈጽሞ አናገኝም።

ማቴዎስ 6:33 ላይ አምላክ ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለሚያስቀድሙ ታማኝ አገልጋዮቹ የሚያስፈልጋቸውን ነገር እንደሚያሟላላቸው ኢየሱስ የሰጠውን ዋስትና እናገኛለን። “እንግዲያው ከሁሉ አስቀድማችሁ የአምላክን መንግሥትና ጽድቅ መፈለጋችሁን ቀጥሉ፤ እነዚህም ነገሮች ሁሉ [ምግብን፣ መጠጥንና ልብስን ጨምሮ] ይሰጧችኋል” በማለት ኢየሱስ በጥብቅ መክሯል። ይሁን እንጂ ኢየሱስ ‘ወንድሞቹ’ በስደት ምክንያት ሊራቡ እንደሚችሉም ገልጿል። (ማቴዎስ 25:35, 37, 40) ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ያለ ሁኔታ አጋጥሞታል። ጳውሎስ የተራበበትና የተጠማበት ጊዜ ነበር።—2 ቆሮ. 11:27

በተለያዩ መንገዶች ስደት እንደሚደርስብን ይሖዋ ነግሮናል። ይሖዋ፣ ሰይጣን ላስነሳው ክስ መልስ ለመስጠት ሲል እንድንቸገር ሊፈቅድ ይችላል። (ኢዮብ 2:3-5) ለምሳሌ ያህል፣ በናዚ ማጎሪያ ካምፖች ታስረው የነበሩ የእምነት አጋሮቻችን በስደት ምክንያት ለሞት በሚያደርስ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ወድቀው ነበር። ዲያብሎስ የይሖዋ ምሥክሮችን ንጹሕ አቋም ለማጉደፍ ከተጠቀመባቸው ዘዴዎች አንዱ ረሃብ ነበር። እነዚህ ታማኝ የይሖዋ ምሥክሮች ለይሖዋ ታዛዥ ነበሩ፤ እሱም አልተዋቸውም። ይሖዋ ሁሉም ክርስቲያኖች የተለያዩ ፈተናዎች እንዲደርሱባቸው እንደሚፈቅድ ሁሉ እነዚህ ወንድሞችም እንዲህ ያለ ፈተና እንዲደርስባቸው ፈቅዷል። ይሁን እንጂ ይሖዋ ለስሙ ሲሉ ሥቃይ የሚደርስባቸውን ሁሉ እንደሚደግፋቸው ጥርጥር የለውም። (1 ቆሮ. 10:13) ሁላችንም በፊልጵስዩስ 1:29 ላይ የሚገኘውን የሚከተለውን ሐሳብ ማስታወስ ይኖርብናል፦ “እናንተ በክርስቶስ እንድታምኑ ብቻ ሳይሆን ለእሱ ስትሉ መከራ እንድትቀበሉም መብት ተሰጥቷችኋል።”

ይሖዋ ከአገልጋዮቹ ጋር እንደሚሆን ቃል ገብቷል። ለምሳሌ ያህል፣ ኢሳይያስ 54:17 “በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል” በማለት ይናገራል። ይህ ጥቅስና ሌሎች ተመሳሳይ ተስፋዎች የአምላክ ሕዝቦች በቡድን ደረጃ ደኅንነታቸው የተጠበቀ እንደሚሆን ዋስትና ይሰጣሉ። በግለሰብ ደረጃ ግን አንድ ክርስቲያን እስከ ሞት ድረስም ጭምር ሊፈተን ይችላል።