በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ሚያዝያ 2014

ይህ እትም እኛም የሙሴ ዓይነት እምነት ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል። እንዲሁም ይሖዋ ለቤተሰብ ኃላፊነት ስላለው አመለካከትና ይህን ግዴታችንን መወጣት እንድንችል የሚረዳን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

እምነት በማሳየት ረገድ ሙሴን ምሰሉ

ሙሴ እምነት ማዳበሩ ሥጋዊ ምኞቶችን እንዲያሸንፍና የአገልግሎት መብቱን ከፍ አድርጎ እንዲመለከት የረዳው እንዴት ነው? ‘የሚከፈለውን ወሮታ በትኩረት የተመለከተውስ’ ለምንድን ነው?

“የማይታየው” አምላክ ይታይሃል?

ሙሴ እምነቱ፣ በሰው ፍርሃት እንዳይሸነፍ እንዲሁም አምላክ ቃል የገባቸው ነገሮች እንደሚፈጸሙ እርግጠኛ እንዲሆን ያደረገው እንዴት ነው? አንተን ለመርዳት የሚጓጓው ይሖዋ እውን እንዲሆንልህ እምነትህን አጠናክር።

የሕይወት ታሪክ

የሙሉ ጊዜ አገልግሎት የከፈተልኝ ግሩም አጋጣሚዎች

ሮበርት ዎለን በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ያሳለፋቸውን 65 ዓመታት መለስ ብሎ ሲያስብ ሕይወቱ የሚክስና ዓላማ ያለው እንደነበር ይሰማዋል። እንዲህ እንዲሰማው ያደረገውን ምክንያት ለማወቅ ተሞክሮውን እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።

ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚችል የለም

አንዳንዶች ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ወደ ውጭ አገር ይሄዳሉ። ለሥራ ሲባል ከቤተሰብ ጋር ተለያይቶ መኖር በትዳር፣ በልጆችና ከአምላክ ጋር ባለን ግንኙነት ላይ ምን ችግር ያስከትላል?

ደፋር ሁን—ይሖዋ ረዳትህ ነው!

አንድ አባት ለሥራ ከተሰደደበት አገር ተመልሶ ወደ ቤተሰቡ በመምጣት ግንኙነታቸውን ለማስተካከል ጥረት ያደረገው እንዴት ነው? በኢኮኖሚ ደካማ በሆነ አገር ውስጥ እየኖረ ቤተሰቡን ማስተዳደር እንዲችል ይሖዋ የረዳው እንዴት ነው?

ይሖዋ የሚመለከተን ለእኛ ጥቅም እንደሆነ ይሰማሃል?

አምላክ እንደሚያስብልን የሚያሳዩ አምስት መንገዶችን ተመልከት፤ እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ትኩረት የሚሰጠን መሆኑ ምን ጥቅም እንደሚያስገኝልን አንብብ።

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በጥንት ዘመን አንድ ሰው ልብሱን መቅደዱ ምን ትርጉም ነበረው?