በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

“አምላክን አውቃችኋል”—ከዚህ በኋላስ?

“አምላክን አውቃችኋል”—ከዚህ በኋላስ?

“አምላክን አውቃችኋል።”—ገላ. 4:9

1. አንድ አብራሪ በረራ ከመጀመሩ በፊት የምርመራ ቅጽ መሙላት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?

አውሮፕላን አብራሪዎች ከበረራ በፊት የሚሞላ ከ30 የሚበልጡ ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ የምርመራ ቅጽ አላቸው። ምንጊዜም በረራ ከመጀመራቸው በፊት ይህን ቅጽ በጥንቃቄ ካልሞሉ አስከፊ የሆነ አደጋ ሊከሰት የሚችልበት አጋጣሚ የሰፋ ይሆናል። አውሮፕላን ለማብረር በተዘጋጁ ቁጥር ይህን ቅጽ እንዲሞሉ ይበልጥ ማሳሰቢያ የሚሰጣቸው የትኞቹ አብራሪዎች እንደሆኑ ታውቃለህ? ብዙ ልምድ ያላቸው አብራሪዎች ናቸው! ተሞክሮ ያካበተ አንድ አብራሪ በቀላሉ ሊዘናጋና የምርመራ ቅጹን በጥንቃቄ ሳይሞላ ሊቀር ይችላል።

2. ክርስቲያኖች ምን ዓይነት ምርመራ ማካሄዳቸው ጠቃሚ ነው?

2 ጠንቃቃ እንደሆነ አንድ አብራሪ አንተም እምነትህ በጣም ወሳኝ በሆነ ሰዓት ላይ እንዳይዳከም እንዲህ ያለ ምርመራ ልታደርግ ትችላለህ። በቅርቡ የተጠመቅክም ሆንክ አምላክን ለበርካታ ዓመታት ስታገለግል የቆየህ ክርስቲያን፣ እምነትህ ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነና ምን ያህል ለይሖዋ አምላክ ያደርክ እንደሆንክ በየጊዜው መመርመርህ በጣም አስፈላጊ ነው። ትጋት በተሞላበት ሁኔታ ይህን ምርመራ አዘውትረን የማናካሂድ ከሆነ መንፈሳዊ ውድቀት ሊደርስብን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ “የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ” ሲል ያሳስበናል።—1 ቆሮ. 10:12

3. በገላትያ የነበሩት ክርስቲያኖች ምን ማድረግ አስፈልጓቸው ነበር?

3 በገላትያ የነበሩት ክርስቲያኖች የእምነታቸውን ጥንካሬ መመርመርና ያገኙትን መንፈሳዊ ነፃነት ከፍ አድርገው መመልከት አስፈልጓቸው ነበር። ኢየሱስ ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ በእሱ የሚያምኑ ሁሉ በጣም ልዩ በሆነ መንገድ አምላክን ማወቅ የሚችሉበትን መንገድ ከፍቷል፤ እነዚህ ሰዎች የአምላክ ልጆች መሆን የሚችሉበትን አጋጣሚ አግኝተዋል! (ገላ. 4:9) የገላትያ ክርስቲያኖች ይህን ልዩ ዝምድና ላለማጣት ከፈለጉ የሙሴን ሕግ መጠበቅ ያስፈልጋል የሚል ጠንካራ አቋም የነበራቸው የአይሁድን እምነት የሚያራምዱ ሰዎች የሚያስተምሩትን ትምህርት ወደ ጎን ገሸሽ ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር። እንዲያውም በክርስቲያን ጉባኤዎች ውስጥ የነበሩት ያልተገረዙ አሕዛብ ቀድሞም ቢሆን ጨርሶ በዚህ ሕግ ሥር  አልነበሩም! አይሁዳውያንም ሆኑ አሕዛብ መንፈሳዊ እድገት ማድረግ ያስፈልጋቸው ነበር። ይህ ደግሞ በሙሴ ሕግ አማካኝነት የራሳቸውን ጽድቅ መመሥረት እንደማይችሉ መገንዘብን ይጨምራል።

አምላክን ለማወቅ ሊወሰዱ የሚገባቸው የመጀመሪያዎቹ እርምጃዎች

4, 5. ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች ምን ምክር ሰጥቷል? ይህ ምክር ለእኛም አስፈላጊ የሆነው እንዴት ነው?

4 ሐዋርያው ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች የሰጠው ምክር በጽሑፍ የሰፈረበት የራሱ የሆነ ዓላማ አለው፤ ይኸውም በየትኛውም ዘመን የሚኖሩ እውነተኛ ክርስቲያኖች ውድ ለሆነው እውነት ጀርባቸውን በመስጠት ትተዋቸው ወደመጡት ነገሮች እንዳይመለሱ መርዳት ነው። ይሖዋ፣ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ምክር በመንፈስ መሪነት እንዲጽፍ ያደረገው በገላትያ የነበሩት ክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆኑ አገልጋዮቹ በሙሉ ጸንተው እንዲኖሩ ለማበረታታት ነው።

5 ሁላችንም ከመንፈሳዊ ባርነት ነፃ ወጥተን የይሖዋ ምሥክሮች የሆንነው እንዴት እንደሆነ መለስ ብለን ማስታወሳችን ጠቃሚ ነው። ይህን ማድረግ ትችል ዘንድ እስቲ የሚከተሉትን ሁለት ጥያቄዎች አስብባቸው፦ ከአንድ እጩ ተጠማቂ የሚጠበቀውን ብቃት ለማሟላት የወሰድካቸውን እርምጃዎች ታስታውሳለህ? አምላክን ልታውቅና አምላክ አንተን ሊያውቅህ የቻለው እንዴት እንደሆነ ብሎም እውነተኛ መንፈሳዊ ነፃነት በማግኘትህ የተሰማህ ደስታ ትዝ ይልሃል?

6. የትኛውን መንፈሳዊ የምርመራ ቅጽ እንመለከታለን?

6 ሁላችንም እውነትን ስንቀበል ዘጠኝ እርምጃዎችን ወስደን ነበር። እነዚህ እርምጃዎች  “ለጥምቀት የሚያበቁና እድገት ማድረጋችንን እንድንቀጥል የሚረዱ እርምጃዎች” የሚል ርዕስ ባለው ሣጥን ውስጥ በዝርዝር የሰፈሩ ሲሆን ራሳችንን በመንፈሳዊ ለመመርመር ያስችሉናል። እነዚህን ዘጠኝ እርምጃዎች ሁልጊዜ ማስታወሳችን ጠንካራ እምነት እንዲኖረንና በዓለም ወዳሉት ነገሮች ከመመለስ እንድንቆጠብ ይረዳናል። ብዙ ልምድ ቢኖረውም እንኳ ጠንቃቃ የሆነ አውሮፕላን አብራሪ በቅድሚያ የምርመራ ቅጹን በመሙላት ለደህንነት አስተማማኝ በሆነ መንገድ በረራውን እንደሚያካሂድ ሁሉ አንተም ይህን መንፈሳዊ የምርመራ ቅጽ መከለስህ ይሖዋን በታማኝነት ማገልገልህን እንድትቀጥል ያስችልሃል።

በአምላክ ዘንድ የታወቁ ሰዎች በመንፈሳዊ ማደጋቸውን ይቀጥላሉ

7. ልንከተለው የሚገባን ንድፍ ምንድን ነው? ለምንስ?

7 አንድ የአውሮፕላን አብራሪ የሚጠቀምበት የምርመራ ቅጽ እያንዳንዱን በረራ ከማካሄዱ በፊት በጥንቃቄ ሊያከናውነው የሚገባ ሥራ እንዳለ እንዲያስታውስ ይረዳዋል። እኛም ራሳችንንም ሆነ ከተጠመቅንበት ጊዜ አንስቶ ስንከተለው የቆየነውን ልማድ አዘውትረን መመርመር እንችላለን። ጳውሎስ “ከእኔ የሰማሃቸውን ጤናማ ቃላት ንድፍ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ዝምድና ካለው እምነትና ፍቅር ጋር ምንጊዜም አጥብቀህ ያዝ” በማለት ለጢሞቴዎስ ጽፎለት ነበር። (2 ጢሞ. 1:13) እነዚህ “ጤናማ ቃላት” የሚገኙት በአምላክ ቃል ውስጥ ነው። (1 ጢሞ. 6:3) አንድ ሠዓሊ ያወጣው ንድፍ ሥዕሉ ምን ሊመስል እንደሚችል ለመረዳት እንደሚያስችለን ሁሉ ‘የእውነት ቃል ንድፍም’ ይሖዋ ከእኛ ምን እንደሚጠብቅ ለማወቅና በዚያ መሠረት ለመመላለስ የሚያስችል አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲኖረን ይረዳናል። በመሆኑም የእውነትን ቃል ንድፍ ምን ያህል በጥብቅ እየተከተልን እንዳለን ለማወቅ ለጥምቀት ያበቁንን እርምጃዎች እስቲ እንመልከት።

8, 9. (ሀ) በእውቀትና በእምነት ማደጋችንን መቀጠል ያለብን ለምንድን ነው? (ለ) መንፈሳዊ እድገት ማድረጋችን ያለውን ጠቀሜታና ይህ እድገት ቀጣይ ሂደት ነው የምንለው ለምን እንደሆነ በምሳሌ አስረዳ።

8 በምርመራ ቅጻችን መጀመሪያ ላይ የሰፈረው እውቀት የመቅሰም አስፈላጊነት ነው። ከዚያ በኋላ እምነት ማዳበር እንችላለን። ይሁንና በሁለቱም ረገድ እድገት ማድረጋችንን መቀጠል ይኖርብናል። (2 ተሰ. 1:3) እድገት ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ለውጦችን ማድረግ ይጠይቃል። “ማደግ” ሲባል መጨመር፣ መስፋፋት ማለት ነው። ስለዚህ ከተጠመቅን በኋላ እድገታችን እንዳይገታ መንፈሳዊነታችንን እያጠናከርን መሄድ አለብን።

አንድ ዛፍ እድገቱ እንደማያቋርጥ ሁሉ ክርስቲያኖችም እድገት ማድረጋቸውን መቀጠል አለባቸው

9 መንፈሳዊ እድገታችን ከአንድ ዛፍ እድገት ጋር ሊመሳሰል ይችላል። አንድ ዛፍ በተለይ ሥሩ ጥልቀት ወይም ስፋት ሲኖረው በጣም ግዙፍ እስኪሆን ድረስ ሊያድግ ይችላል። ለምሳሌ ያህል ግርማ ሞገስ የተላበሱ አንዳንድ የአርዘሊባኖስ ዛፎች ቁመታቸው 12 ፎቅ ካለው ሕንፃ ርዝመት ጋር ሊተካከል ይችላል፤ በተጨማሪም ወደታች ጠልቀው የሚገቡ ጠንካራ ሥሮች ያሏቸው ሲሆን የግንዶቻቸው መጠነ ዙሪያ እስከ 12 ሜትር ሊደርስ ይችላል። (ማሕ. 5: 15 NW) እንዲህ ያለ ዛፍ መጀመሪያ ላይ ፈጣን እድገት አድርጎ ካበቃም በኋላ ጉልህ በሆነ መንገድ ባይሆንም እንኳ እድገት ማድረጉን ይቀጥላል። ዓመታት እያለፉ በሄዱ መጠን ግንዱ እየወፈረ እንዲሁም ሥሮቹ ጥልቀታቸውና ስፋታቸው እየጨመረ ይሄዳል፤ ይህም ዛፉ ይበልጥ ጸንቶ እንዲቆም ያስችለዋል። የአንድ ክርስቲያን መንፈሳዊ እድገትም ተመሳሳይ ነው። መጀመሪያ ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና ፈጣን መንፈሳዊ እድገት አድርገን ልንጠመቅ እንችላለን። የጉባኤያችን አባላት የምናደርገውን እድገት በማየት ይደሰታሉ። እንዲያውም አቅኚ ልንሆን አሊያም ሌሎች መብቶችን ልናገኝ እንችላለን። ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ቀጣይ የሆነው መንፈሳዊ እድገታችን ያን ያህል ጎልቶ አይታይ ይሆናል። ያም ሆኖ “ሙሉ ሰው ወደ መሆንና ክርስቶስ ወዳለበት የሙላት ደረጃ እስክንደርስ” በእምነትና በእውቀት ማደጋችንን መቀጠላችን አስፈላጊ ነው። (ኤፌ. 4:13) በዚህ መንገድ በምሳሌያዊ ሁኔታ ከአንዲት ትንሽ ቡቃያ ተነስተን እድገት በማድረግ ጠንካራና ትልቅ ወደሆነ ዛፍ ልንሸጋገር ማለትም የጎለመስን ክርስቲያኖች ልንሆን እንችላለን።

10. የጎለመሱ ክርስቲያኖችም እንኳ እድገት ማድረጋቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

10 ይሁንና እድገታችን በዚህ ማብቃት የለበትም። እውቀታችን እየዳበረ፣ እምነታችንም እየጠነከረ መሄድ ይኖርበታል። በዚህ መንገድ በአምላክ ቃል አፈር ውስጥ ከምንጊዜውም በበለጠ ሁኔታ ጽኑ ሆነን እንተከላለን። (ምሳሌ 12:3) በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ወንድሞችና እህቶች ይህን ማድረግ ችለዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ከሠላሳ ዓመታት በላይ ሽማግሌ ሆኖ ያገለገለ አንድ ወንድም አሁንም በመንፈሳዊ በማደግ ላይ መሆኑን ገልጿል። እንዲህ ብሏል፦ “ለመጽሐፍ ቅዱስ ያለኝ አድናቆት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል። በየጊዜው የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶችና ሕጎች በተለያዩ መንገዶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ ሁኔታዎች ያጋጥሙኛል። ለአገልግሎት ያለኝ አድናቆትም እያደገ ሄዷል።”

ከአምላክ ጋር የመሠረታችሁትን ወዳጅነት አጠናክሩ

11. ይሖዋን በጊዜ ሂደት ይበልጥ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?

11 እድገት ማድረጋችንን መቀጠል ከፈለግን ይሖዋን እንደ ወዳጅና እንደ አባት አድርገን በመመልከት ወደ እሱ ይበልጥ መቅረብ ይኖርብናል። በእሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለንና እንደምንወደድ እንዲሁም የእሱን ጥበቃ እንደምናገኝ እንዲሰማን ይፈልጋል። አንድ ልጅ አፍቃሪ በሆነው ወላጁ እቅፍ ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ የሚሰማው ዓይነት ስሜት ወይም እኛ ራሳችን ከአንድ ታማኝ ጓደኛችን ጋር በምንሆንበት ጊዜ የሚሰማን ዓይነት ስሜት እንዲሰማን ይፈልጋል። በአንድ ጀምበር ከይሖዋ ጋር እንዲህ ያለ የጠበቀ ወዳጅነት መመሥረት እንደማይቻል የታወቀ ነው። እሱን ማወቅና መውደድ የምንችለው በጊዜ ሂደት ነው። በመሆኑም የይሖዋን ማንነት ይበልጥ ማወቅ ትችል ዘንድ ቃሉን በየዕለቱ ለማንበብ ጊዜ መድብ። እንዲሁም እያንዳንዱን የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት እትም ብሎም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎችን አንብብ።

12. በይሖዋ ዘንድ መታወቅ የምንፈልግ ከሆነ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

12 የአምላክ ወዳጆች ልባዊ ጸሎት በማቅረብና ጥሩ  ወዳጅነት በመመሥረት በመንፈሳዊ እድገት ያደርጋሉ። (ሚልክያስ 3:16ን አንብብ።) የይሖዋ ‘ጆሮዎች ምልጃቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው።’ (1 ጴጥ. 3:12) ይሖዋ ልክ እንደ አንድ አፍቃሪ ወላጅ፣ በጸሎት አማካኝነት እርዳታ ለማግኘት የምናሰማውን ጩኸት በትኩረት ያዳምጣል። በመሆኑም ‘በጽናት መጸለይ’ ያስፈልገናል። (ሮም 12:12) የአምላክን እርዳታ ካላገኘን የጎለመስን ክርስቲያኖች ሆነን መቀጠል አንችልም። ይህ ሥርዓት የሚያሳድርብንን ከባድ ተጽዕኖ በራሳችን ብርታት ለመቋቋምና ለማሸነፍ የሚያስችል አቅም አይኖረንም። በጽናት የምንጸልይ ከሆነ አምላክ ለእኛ ብርታት ለመስጠት ፈቃደኛ ነው። የጸሎትህ ይዘት ጥሩ እንደሆነ ይሰማሃል ወይስ በዚህ ረገድ ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልግሃል?—ኤር. 16:19

13. መንፈሳዊ እድገት ለማድረግ ከክርስቲያን ባልንጀሮቻችን ጋር መሰብሰባችን በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

13 ይሖዋ ‘በሚታመኑበት’ ሰዎች ደስ ይሰኛል፤ በመሆኑም አምላክን ካወቅን በኋላም እንኳ እሱን ከሚያውቁ ሌሎች ሰዎች ጋር አዘውትረን መሰብሰባችንን መቀጠል ይኖርብናል። (ናሆም 1:7) ተስፋ በሚያስቆርጡ ሁኔታዎች በተሞላው ዓለም ውስጥ ሊያበረታቱን ከሚችሉ ወንድሞችና እህቶች ጋር መቀራረባችን ጥበብ ነው። እንዲህ ማድረጋችን ምን ጥቅሞች ያስገኝልናል? በጉባኤ ውስጥ “ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች” የሚያነቃቁ ሰዎችን ታገኛለህ። (ዕብ. 10:24, 25) ጳውሎስ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች በጻፈው መሠረት አንዳችን ለሌላው ፍቅር ለማሳየት በአንድ የወንድማማች ማኅበር ይኸውም አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ያላቸው አምላኪዎች በተሰባሰቡበት ጉባኤ መታቀፍ አለብን። እንዲህ ያለውን ፍቅር ለማሳየት ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር መገናኘትና አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ይጠይቃል። ቅጹን ተጠቅመህ ራስህን በምትመረምርበት ጊዜ አዘውትረህ በስብሰባዎች ላይ ስለመገኘትህና ተሳትፎ ስለማድረግህ እርግጠኛ ሁን።

14. ንስሐ መግባትና መመለስ ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?

14 መጀመሪያ ላይ ክርስቲያን በሆንበት ጊዜ ንስሐ መግባት እና ከኃጢአት ድርጊቶቻችን መመለስ ወይም እነዚህን ድርጊቶች እርግፍ አድርገን መተው አስፈልጎን ነበር። ይሁን እንጂ ንስሐ መግባት ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው። ፍጹም ያልሆንን ሰዎች እንደመሆናችን መጠን ኃጢአት ለመናደፍ እንደተዘጋጀ እባብ በውስጣችን አድብቶ ይጠብቃል። (ሮም 3:9, 10፤ 6:12-14) ድክመቶቻችንን ችላ ከማለት ይልቅ ንቁዎች መሆን ይኖርብናል። ድክመቶቻችንን ለማሸነፍና አስፈላጊውን ለውጥ ለማድረግ ከልባችን ስንጥር ይሖዋ በትዕግሥት እንደሚይዘን ማወቁ ያስደስታል። (ፊልጵ. 2:12፤ 2 ጴጥ. 3:9) ጊዜያችንን እና ጥሪታችንን የራሳችንን ጥቅም ለማሳደድ ከማዋል ይልቅ በተሻለ መንገድ ልንጠቀምበት ይገባል። አንዲት እህት እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “በእውነት ቤት ውስጥ ያደግኩ ብሆንም ይሖዋን በተመለከተ ከብዙዎቹ የተለየ አመለካከት ነበረኝ። በጣም የሚፈራ አምላክ እንደሆነ አድርጌ አስብ ነበር፤ እንዲሁም እሱን ማስደሰት ፈጽሞ የማይቻል ነገር እንደሆነ ይሰማኝ ነበር።” ከጊዜ በኋላ ይህች እህት የተለያዩ እንቅፋቶች ስለገጠሟት “በመንፈሳዊ ተዳከመች።” አክላም እንዲህ ብላለች፦ “ይህ የሆነው ይሖዋን ስለማልወደው አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ ይሖዋን በሚገባ አላውቀውም ነበር። ይሁንና በተደጋጋሚ አጥብቄ ከጸለይኩ በኋላ ለውጥ ማድረግ ጀመርኩ።” ደግሞም “ይሖዋ እንደ አንድ ትንሽ ልጅ እጄን ይዞ በቀስታ እየመራ እያንዳንዱን እንቅፋት ደረጃ በደረጃ ማለፍ እንድችል በመርዳት ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንድገነዘብ አድርጎኛል።”

15. ኢየሱስና አባቱ ምን ነገር በትኩረት ይከታተላሉ?

15 ምሥራቹን “ለሕዝቡ መናገራችሁን ቀጥሉ።” የአምላክ መልአክ ለጴጥሮስና ለሌሎቹ ሐዋርያት እንዲህ ብሎ የተናገረው በተአምራዊ ሁኔታ ከእስር ቤት ከተለቀቁ በኋላ ነበር። (ሥራ 5:19-21) አዎ፣ መንፈሳዊ ምርመራ በምናደርግበት ቅጽ ላይ የሰፈረው ሌላው ነጥብ በየሳምንቱ በመስክ አገልግሎት የምናደርገው ተሳትፎ ነው። ኢየሱስና አባቱ እምነታችንንም ሆነ አገልግሎታችንን በትኩረት ይከታተላሉ። (ራእይ 2:19) ቀደም ሲል የተጠቀሰው ሽማግሌ እንዳለው “የመስክ አገልግሎት ዋነኛ ሥራችን ነው።”

16. ራሳችንን ለይሖዋ በመወሰን የወሰድነውን እርምጃ ማሰባችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

16 ራስህን ለአምላክ በመወሰን የወሰድከውን እርምጃ አስብ። ከምንም ነገር በላይ ውድ የሆነው ሀብታችን ከይሖዋ ጋር የመሠረትነው የግል ዝምድና ነው። ይሖዋ የእሱ የሆኑትን ያውቃል። (ኢሳይያስ  44:5ን አንብብ።) ከእሱ ጋር ያለህ ዝምድና ምን ያህል ጠንካራና የጠበቀ እንደሆነ በጸሎት አስብበት። ከዚህ ጋር በተያያዘ ደግሞ በሕይወት ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውን የጥምቀትህን ቀን አስታውስ። ይህም ጥምቀትህ እስከ ዛሬ ካደረግካቸው ውሳኔዎች ሁሉ የላቀ ትርጉም እንዳለው እንድታስታውስ ይረዳሃል።

በጽናት ከይሖዋ ጋር ተቀራርባችሁ ኑሩ

17. ከይሖዋ ጋር ተቀራርበን ለመኖር ጽናት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

17 ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች ሲጽፍ የጽናትን አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ ገልጿል። (ገላ. 6:9) በዛሬው ጊዜም ጽናት ለአንድ ክርስቲያን በጣም አስፈላጊ ነው። ፈተናዎች እንደሚያጋጥሙህ እሙን ነው፤ ሆኖም ይሖዋ ይረዳሃል። መንፈስ ቅዱስን ለማግኘት ጸልይ። አምላክ በሚሰጥህ እርዳታ ሐዘንህ በደስታ፣ ጭንቀትህ በሰላም ሲተካ እፎይታ ታገኛለህ። (ማቴ. 7:7-11) እስቲ ቆም ብለህ ለማሰብ ሞክር፦ ይሖዋ ወፎችን የሚንከባከባቸው ከሆነ እሱን የምትወደውንና ራስህን ለእሱ አሳልፈህ የሰጠኸውን አንተን ይበልጥ አይንከባከብህም? (ማቴ. 10:29-31) ምንም ዓይነት ተጽዕኖ ቢደርስብህ ፈጽሞ ወደኋላ አታፈግፍግ፤ ደግሞም ተስፋ አትቁረጥ። በይሖዋ ዘንድ መታወቃችን እንዴት ያሉ ግሩም በረከቶች ያስገኝልናል!

18. ‘አምላክን ያወቅክ’ እንደመሆንህ መጠን ከዚህ በኋላስ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

18 እንግዲያው አምላክን አውቀህ የተጠመቅከው በቅርቡ ከሆነ ከዚህ በኋላስ ምን ማድረግ ይኖርብሃል? ይሖዋን ይበልጥ ለማወቅ ጥረት በማድረግ በመንፈሳዊ ማደግህን ቀጥል። ወይም ደግሞ ከተጠመቅክ ብዙ ዓመታት አልፈው ሊሆን ይችላል፤ ከሆነ ምን ማድረግ ይኖርብሃል? በዚህ ጊዜም ቢሆን ስለ ይሖዋ ያለህን እውቀት ይበልጥ እያሳደግክና እያዳበርክ መሄድህ አስፈላጊ ነው። ከይሖዋ ጋር ባለን ዝምድና ረገድ ፈጽሞ ቸልተኞች መሆን የለብንም። ከዚህ ይልቅ አፍቃሪ አባት፣ ወዳጅና አምላክ ከሆነው ከይሖዋ ጋር ያለንን ዝምድና እያጠናከርን መሄድ እንድንችል ሁላችንም መንፈሳዊ ምርመራ የምናካሂድበትን ቅጽ በየጊዜው መከለስ ይኖርብናል።—2 ቆሮንቶስ 13:5, 6ን አንብብ።