በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም የካቲት 2013

ይህ መጽሔት የይሖዋ ሕዝቦች በመሆናችን ስላገኘነው መንፈሳዊ ውርሻ ያብራራል። በተጨማሪም ከይሖዋ ጥበቃ ሳንወጣ መኖር የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንድትመረምር እንጋብዛሃለን።

ይህ መንፈሳዊ ውርሻችን ነው

ይሖዋ ለመላው የሰው ዘር እና ለሕዝቦቹ ያደረገውን በመመርመር ለመንፈሳዊ ውርሻችን ያለህ አድናቆት እንዲጨምር አድርግ።

ለመንፈሳዊ ውርሻችን አድናቆት አላችሁ?

ስለ መንፈሳዊ ውርሻችን ማወቅህ እንዲሁም ይህን ውርሻ ከፍ አድርገህ መመልከትህ ለአምላክ ታማኝ ሆነህ ለመኖር ያደረግኸውን ቁርጥ ውሳኔ ያጠናክርልሃል።

የንጉሠ ነገሥቱ የክብር ዘብ አባላት ምሥራቹን ሰሙ

ጳውሎስ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅሞ ምሥክርነት ይሰጥ ነበር። እሱ የተወው ምሳሌ አንተም እንዲህ ማድረግ እንድትችል የሚረዳህ እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ጥበቃ ከምታገኙበት ከይሖዋ ሸለቆ አትውጡ

ጥበቃ የሚገኝበት ሸለቆ ምንድን ነው? የይሖዋ አገልጋዮች በዚህ ሸለቆ ውስጥ ጥበቃ ማግኘት የሚችሉትስ እንዴት ነው?

ልብህ እንዳያታልልህ ተጠንቀቅ

አንዳንድ ጊዜ ልባችን የተሳሳተ ድርጊት ለመፈጸም ሰበብ እንድንፈጥር ሊያደርገን ይችላል። ታዲያ በልባችን ውስጥ ያለው ምን እንደሆነ በትክክል ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?

የአምላክን ክብር እንዳታገኙ ምንም ነገር እንቅፋት አይሁንባችሁ

አምላክ የሚሰጠውን ክብር ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው? ይህን ክብር እንዳታገኝ እንቅፋት ሊሆኑብህ የሚችሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

የቀያፋ ቤተሰብ የሆነች ሴት

የሚርያም የአፅም ማስቀመጫ ሣጥን መገኘቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎችም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው በታሪክ ውስጥ በእርግጥ የነበሩ እንደሆኑ ያረጋግጣል።

ከታሪክ ማኅደራችን

ወቅታዊ የሆነ “ፈጽሞ የማይረሳ” ፊልም

አዲሱ የፍጥረት ድራማ፣ በጀርመን የነበሩ የይሖዋ ምሥክሮች በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ወቅት የደረሰባቸውን የእምነት ፈተና እንዲቋቋሙ የረዳቸው እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።