በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ንቁ!  |  መስከረም 2015

 ከዓለም አካባቢ

የዜናው ትኩረት—መካከለኛው ምሥራቅ

የዜናው ትኩረት—መካከለኛው ምሥራቅ

በአንድ ወቅት የአብዛኞቹ የዓለማችን ቀደምት ሥልጣኔዎች መናኸሪያ የነበረው መካከለኛው ምሥራቅ ለብዙ የአርኪኦሎጂ ግኝቶች ምንጭ ነው።

ከነአናውያን ወይን ጠማቂዎች

በ2013 የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች ከ3,700 ዓመታት በፊት የነበረ የከነአናውያን ትልቅ የወይን ጠጅ መጋዘን አግኝተዋል። በመጋዘኑ ውስጥ 3,000 ዘመናዊ የወይን ጠጅ ጠርሙሶች የሚያህል ወይን የሚይዙ 40 ትላልቅ እንስራዎች ተገኝተዋል። እንስራዎቹ ውስጥ በተገኘው የወይን ጠጅ ዝቃጭ ላይ ምርምር ያደረጉ አንድ የአርኪኦሎጂ ባለሙያ ከነአናውያን ጥሩ የወይን ጠጅ ጠማቂዎች እንደነበሩ መረዳት ችለዋል። “እያንዳንዱ እንስራ ውስጥ የነበረው የወይን ጠጅ ተመሳሳይ በሆነ መንገድ በጥንቃቄ የተቀመመ ነው” በማለት ተናግረዋል።

ይህን ያውቁ ኖሯል? መጽሐፍ ቅዱስ በጥንቷ እስራኤል “ምርጥ ወይን ጠጅ” ተዘጋጅቶ በትላልቅ እንስራዎች ውስጥ ይቀመጥ እንደነበር ይናገራል።—መኃልየ መኃልይ 7:9፤ ኤርምያስ 13:12

የሕዝብ ቁጥር መጨመር

ጋርዲያን የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው በ2012 በግብፅ የተወለዱ ሕፃናት በ2010 ከተወለዱት ሕፃናት ቁጥር 560,000 ያህል ይበልጣል። “ይህ በግብፅ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ቁጥር ነው” ሲሉ ባሴራ የተባለው የግብፅ የምርምር ኩባንያ ባልደረባ የሆኑት ማጌድ ኦስማን ተናግረዋል። ጭማሪው በዚሁ ከቀጠለ አገሪቱ ከአሁኑ የከፋ የውኃ፣ የኃይልና የምግብ እጥረት እንደሚያጋጥማት አንዳንድ ባለሙያዎች ገልጸዋል።

ይህን ያውቁ ኖሯል? መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ለሰው ልጆች ያለው ዓላማ ‘ምድርን እንዲሞሏትና’ ምንም ሳይጣበቡ ፍላጎታቸው ሁሉ ተሟልቶላቸው እንዲኖሩ መሆኑን ይናገራል።—ዘፍጥረት 1:28፤ መዝሙር 72:16

የተከማቹ ሳንቲሞች ተገኙ

እስራኤል ውስጥ “አራተኛ ዓመት” የሚል ጽሑፍ የተቀረጸባቸው ከ100 በላይ የሚሆኑ የነሐስ ሳንቲሞች አንድ አውራ ጎዳና አቅራቢያ ተገኙ። እዚህ ላይ የተጠቀሰው ጊዜ አይሁዳውያን በሮማውያን ላይ ያመፁበትን (ኢየሩሳሌምን ለውድቀት የዳረጋት ዓመፅ) አራተኛ ዓመት (69-70 ዓ.ም.) ያመለክታል። “ምናልባት አንድ ሰው እየገሰገሰ ያለውን የሮም ሠራዊት ሲመለከት መጨረሻው እንደቀረበ ስለተሰማው . . . አካባቢው ሲረጋጋ ተመልሶ ሊወስደው እንደሚችል በማሰብ ንብረቱን እንደሸሸገ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል” በማለት የቁፋሮው አስተባባሪ የሆኑት ፓብሎ ቤትሴር ተናግረዋል።

ይህን ያውቁ ኖሯል? በ33 ዓ.ም. ኢየሱስ ሮማውያን ኢየሩሳሌምን እንደሚከቡ ተንብዮ ነበር። ክርስቲያኖች ሕይወታቸውን ማትረፍ ከፈለጉ ወደ ተራሮች እንዲሸሹ አሳስቧቸው ነበር።—ሉቃስ 21:20-24