በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ንቁ!  |  ሰኔ 2014

 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሞት

ሞት

ሙታን የት ናቸው?

“ዐፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ።”—ዘፍጥረት 3:19

ሰዎች ምን ይላሉ?

አንዳንዶች፣ ሰዎች ከሞቱ በኋላ ሰማይ ወይም ገሃነመ እሳት አሊያም መንጽሔ እንደሚገቡ ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ ሌላ ዓይነት ፍጥረት ሆነው ዳግም እንደሚወለዱ ያምናሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን የማይቀበሉ ሰዎች፣ ሞት የሁሉ ነገር ፍጻሜ እንደሆነ ይናገራሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መክብብ 9:10 “ልትሄድበት ባለው መቃብር ውስጥ መሥራትም ሆነ ማቀድ፣ ዕውቀትም ሆነ ጥበብ የለም” ይላል። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎችም ሆኑ እንስሳት በሚሞቱበት ጊዜ ምን እንደሚሆን ይገልጻል። እንዲህ ይላል፦ “ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ፤ ሁሉም ከዐፈር እንደ ሆኑ፣ ተመልሰው ወደ ዐፈር ይሄዳሉ።”—መክብብ 3:20

 ሙታን ምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ?

“መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤ ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር ይሆናል።”—መዝሙር 146:4

ሰዎች ምን ይላሉ?

ብዙ ሰዎች፣ አንድ ሰው ከሞተ በኋላ የሚደርስበት ነገር ምድር ሳለ ባከናወናቸው ነገሮች ላይ የተመካ እንደሆነ ተምረዋል። ጥሩ ሥራ ሠርቶ ካለፈ ለዘላለም በደስታ ይኖራል፤ መጥፎ ሰው ከነበረ ግን ለዘላለም ይሠቃያል። የሰው ልጆች ከሞቱ በኋላ አምላክ ዘንድ ከመቅረባቸው በፊት ከኃጢአታቸው መንጻት እንደሚያስፈልጋቸው ይነገራል። ከኃጢአታቸው ያልነጹ ሁሉ ይህን ደስታ ለዘላለም ሳያገኙ ይቀራሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሙታን ሊደሰቱም ሆነ ሊሠቃዩ አይችሉም። ከሕልውና ውጪ ስለሆኑ ምንም ስሜት የላቸውም፤ በሕይወት ያሉትን ሊጎዱም ሆነ ሊጠቅሙ አይችሉም። መክብብ 9:5, 6 እንዲህ ይላል፦ “ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁምና፤ . . . ፍቅራቸው፣ ጥላቻቸው፣ ቅናታቸውም ከጠፋ ቈይቶአል፤ ከፀሓይ በታች በሚሆነው ነገር ሁሉ፣ ፈጽሞ ዕጣ ፈንታ አይኖራቸውም።”

ታዲያ ሙታን ተስፋ አላቸው?

“ሰው ከሞተ በኋላ ተመልሶ በሕይወት ይኖራል? እድሳቴ እስከሚመጣ ድረስ፣ ተጋድሎ የሞላበትን ዘመኔን ሁሉ እታገሣለሁ።”—ኢዮብ 14:14

ሰዎች ምን ይላሉ?

አንድ ሰው ገሃነመ እሳት ውስጥ እንዲገባ ከተፈረደበት ከዚያ በኋላ ምንም ተስፋ እንደሌለው ይታመናል። ገሃነመ እሳት ውስጥ ለዘላለም እንደሚሠቃይ ይነገራል። በመንጽሔ ውስጥ የሚገኙት ግን ኃጢአታቸው በእሳት ከጠራ በኋላ በሰማይ በመኖር ይደሰታሉ ተብሎ ይታመናል።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

የአምላክ ልጅ፣ በሞት ያንቀላፉ ሰዎችን ወደ ሕይወት በመመለስ ምድር ላይ እንዲኖሩ ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ ‘በዚህ አትደነቁ፤ መቃብር ውስጥ ያሉ ሁሉ ድምፁን ሰምተው የሚወጡበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል። (ዮሐንስ 5:26, 28, 29) አምላክ ለእነዚህ ሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠቱና አለመስጠቱ የተመካው ከሞት ከተነሱ በኋላ በሚያሳዩት ምግባር ላይ ነው። *

^ አን.14 ትንሣኤን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 7 ተመልከት፤ ይህ መጽሐፍ www.jw.org/am ላይም ይገኛል።