በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ንቁ! ሚያዝያ 2014 | መኖር ምን ዋጋ አለው?—ዋጋ እንዳለው የሚያሳዩ ሦስት ምክንያቶች

አንተ ራስህ ወይም የምታውቀው ሌላ ሰው ራስን ስለ ማጥፋት አስባችሁ ታውቃላችሁ? መኖርን እንድትመርጥ የሚያደርግ ምክንያት ብታገኝ አመለካከትህ እንደሚቀየር ምንም ጥያቄ የለውም።

ከዓለም አካባቢ

ከርዕሰ ጉዳዮቹ መካከል፦ አንዲት ከተማ የትራፊክ መብራቶች ተቀናጅተው እንዲሠሩ ማድረጓ፣ በቂ ምግብ ካለማግኘት የሚከፋ የጤና ችግር መኖሩ እንዲሁም ከ60 ዓመት የሚበልጥ ዕድሜ ያላት አንዲት የዱር ወፍ ጫጩት መፈልፈሏ።

ለቤተሰብ

የሚሰጥህን እርማት እንዴት ልትቀበል ይገባል?

ስሜትህን እንደጎዳ የተሰማህ ምክር ወይም እርማት እንዲያውም በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፤ እንዴት?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

መኖር ምን ዋጋ አለው?

አንድ ሰው ሞትን እንዲመኝ የሚያደርገው ምን ሊሆን ይችላል?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ሁኔታዎች ይለወጣሉ

ያለህበት ሁኔታ ሊለወጥ ባይችልም እንኳ ልትለውጠው የምትችለው ነገር አለ።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

እርዳታ ማግኘት ይቻላል

በሕይወት መኖርን እንድትመርጥ የሚያደርግ እርዳታ ከሦስት አቅጣጫዎች ማግኘት ትችላለህ።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ተስፋ አለ

ከአድማስ ባሻገር የሚታይ ውጋገን የጨለማውን መገፈፍ እንደሚጠቁም ሁሉ ተስፋም ካለህበት የጨለማ ሕይወት የምትወጣበትን ጊዜ አሻግረህ እንድትመለከት ይረዳሃል።

ቃለ ምልልስ

‘ፈጣሪ ስለ መኖሩ እርግጠኛ ሆንኩ’

ፍሬድሪክ ዱሙላ ለሃይማኖት ጥላቻ ስላደረበት አምላክ የለሽ ሆኖ ነበር። ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱና ሕይወት ባላቸው ነገሮች ላይ ምርምር ማድረጉ ፈጣሪ መኖሩን ያሳመነው እንዴት ነው?

አገሮችና ሕዝቦች

ካምቦዲያን እንጎብኝ

ቀደም ሲል ተገናኝተው የማያውቁ ሰዎች ወንድም፣ እህት፣ አክስት፣ አጎት፣ ወይም አያት በመባባል የሚጠራሩት ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ዘረኝነት

ሁሉም ዘሮች እኩል ናቸው? ዘረኝነት የማይኖርበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

ንድፍ አውጪ አለው?

የቢራቢሮ ክንፍ

ብሉ ሞርፎ የተባለው ቢራቢሮ ክንፍ እንዲሁ ሲታዩ ልሙጥ ይምሰሉ እንጂ በአጉሊ መነጽር ብቻ የሚታዩ የተነባበሩ ቅርፊቶች አሉት። ዓላማቸው ምንድን ነው?

በተጨማሪም . . .

ስለ ሴክስቲንግ ምን ማወቅ ይኖርብኛል?

እርቃን የሚያሳዩ ፎቶግራፎች እንድትልኪ ተጽዕኖ ይደረግብሻል? ሴክስቲንግ የሚያስከትለው ጉዳት ምንድን ነው? ሴክስቲንግ ምንም ጉዳት የማያስከትል የፍቅር መግለጫ ነው?

ብቸኝነት የሚሰማኝ ቢሆንስ?

ብቸኝነትን ለማሸነፍና ዘላቂ ጓደኝነት ለመመሥረት የሚረዱ ሦስት ነጥቦችን ተመልከት።

ጉልበተኞች ቢያስቸግሩኝ ምን ላድርግ?

ጉልበተኞች የሚያስቸግሯቸው ብዙ ልጆች ማንም ሊረዳቸው እንደማይችል ይሰማቸዋል። ይህን ሁኔታ ለመቋቋም ምን ማድረግ እንደሚቻል በዚህ ርዕስ ላይ ይብራራል።

እውነተኛ ጓደኛ የሚባለው ምን ዓይነት ጓደኛ ነው?

አስመሳይ ጓደኛ ማግኘት ቀላል ነው፤ ይሁን እንጂ እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

ዮሴፍ የሰዎችን ሕይወት አትርፏል

ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚረዱ መልመጃዎችን በመጠቀም ዘፍጥረት ምዕራፍ 41 እስከ 50 ያሉትን ምዕራፎች በቤተሰብ ደረጃ መርምሩ።