በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ንቁ! ጥቅምት 2013 | በገንዘብ ሊገዙ የማይችሉ ሦስት ነገሮች

ንብረት የማካበት አባዜ ከተጠናወተን በሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ይኸውም በገንዘብ ሊገዙ የማይችሉትን ነገሮች ልናጣ እንችላለን። ከእነዚህ ነገሮች መካከል ሦስቱን እንደ ምሳሌ እንመልከት።

ከዓለም አካባቢ

ከርዕሰ ጉዳዮቹ መካከል፦ የቻይና የትራፊክ መጨናነቅ፣ የአርሜንያ መንግሥት የሃይማኖት ነፃነትን መጋፋቱ፣ በጃፓን ማኅበራዊ ድረ ገጾች እያስከተሉት ያለው አደጋ እና ሌሎችም።

ለቤተሰብ

ጓደኝነት ገደቡን ሲያልፍ

‘ከጓደኝነት ያለፈ ምንም ነገር የለንም’ ብላችሁ ታስባላችሁ? ይህ ዓይነቱ አመለካከት ትክክል መሆን አለመሆኑን ለማወቅ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን መርምሩ።

ቃለ ምልልስ

የባዮኬሚስትሪ ባለሙያ ስለሚያምንበት ነገር ምን ይላል?

አንድ የሳይንስ ተመራማሪ ስለ ሕይወት አመጣጥ ያለውን አመለካከት መለስ ብሎ እንዲያጤን እና መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል መሆኑን እንዲያምን ያደረገው ምንድን ነው?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

በገንዘብ ሊገዙ የማይችሉ ሦስት ነገሮች

አንዳንድ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለመግዛት ገንዘብ ያስፈልገናል፤ ነገር ግን በሕይወታችን ከሁሉ የበለጠ እርካታ የሚያስገኙልን፣ በገንዘብ ሊገዙ የማይችሉ ነገሮች ናቸው።

የሚጥል በሽታ—ልታውቀው የሚገባው ነገር

ብዙ ሰዎች ስለዚህ የጤና እክል የተሳሳተ አመለካከት አላቸው፤ እስቲ ይህን የጤና እክል አስመልክቶ አንዳንድ መሠረታዊ ነገሮችን እንመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

የመንፈስ ጭንቀት

ሰዎች በመንፈስ ጭንቀት የሚጠቁት ለምን እንደሆነ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ አሉታዊ ስሜቶችን ለማስወገድ እንዴት እንደሚረዳህ እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።

ንድፍ አውጪ አለው?

አስደናቂ የሆነው የእንጭርሪት የመስማት ችሎታ

የዚህች ትንሽ ነፍሳት ጆሮ የሚሠራው፣ የሰው ልጆች ጆሮ ከሚሠራበት መንገድ ጋር በሚመሳሰል መልኩ ነው። ስለዚህች ነፍሳት ልዩ የሆነ የመስማት ችሎታ የሚደረገው ምርምር ለዘመናዊው ሳይንስ እና ምሕንድስና አስተዋጽኦ የሚያበረክተው እንዴት ነው?

በተጨማሪም . . .

ጉልበተኞች ቢያስቸግሩህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

ጉልበተኞች የሚያስቸግሯቸው ብዙ ልጆች ማንም ሊረዳቸው እንደማይችል ይሰማቸዋል። ይህን ሁኔታ ለመቋቋም ምን ማድረግ እንደሚቻል በዚህ ርዕስ ላይ ይብራራል።

ስለ መልክሽ ከልክ በላይ ትጨነቂያለሽ?

መልክሽን የማትወጂው ከሆነ፣ ሚዛናዊ አመለካከት ማዳበር የምትችዪው እንዴት ነው?

የጤና ችግር ቢኖርብኝ ምን ላድርግ?—ክፍል 1

አራት ወጣቶች ያለባቸውን የጤና ችግር ለመቋቋምና አዎንታዊ አመለካከት ለመያዝ የረዳቸው ምን እንደሆነ ተናግረዋል።

ወጣቶች ስለ ቁመና ምን ይላሉ?

ወጣቶች ስለ መልክ ሚዛናዊ አመለካከት መያዝ ከባድ የሚሆንባቸው ለምን ሊሆን ይችላል? በዚህ ረገድ ምን ሊረዳቸው ይችላል?

የእንጀራ ቤቱ አዛዥ ሕልም

ይህን የሥዕል መልመጃ አውርደህ አትመው፤ ከዚያም የእንጀራ ቤቱን አዛዥ ሕልም በሚያሳዩት ሁለት ሥዕሎች መካከል ያሉትን ልዩነቶች ፈልግ።