በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ንቁ!  |  ቁጥር 1 2016

 አገሮችና ሕዝቦች

ሊክቴንስታይንን እንጎብኝ

ሊክቴንስታይንን እንጎብኝ

ሊክቴንስታይን በዓለማችን ካሉ ትናንሽ አገሮች ውስጥ አንዷ ስትሆን በስዊዘርላንድና በኦስትሪያ መካከል በአልፕስ ተራሮች ላይ ትገኛለች። ባለፉት ዘመናት በዚህ አካባቢ ኬልቶች፣ ሪሸናውያን፣ ሮማውያንና አለማኒዎች ኖረዋል። በአሁኑ ጊዜ ካሉት የሊክቴንስታይን ነዋሪዎች መካከል ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት ከ1,500 ዓመታት በፊት በዚህ ቦታ ላይ ይኖሩ የነበሩ የአለማኒ ጎሳ ተወላጆች ናቸው።

የሊክቴንስታይን የሥራ ቋንቋ ጀርመንኛ ቢሆንም ቋንቋውን የሚነገርበት መንገድ ከመንደር መንደር ይለያያል። የሊክቴንስታይን ነዋሪዎች ከሚወዷቸው ምግቦች መካከል ከበቆሎ የሚዘጋጀው ትዩርካሬብል እና አስክኖፍል (ፓስታ በቺዝ) ይገኙበታል።

አስክኖፍል

በቀለማት ያሸበረቀ የባሕል ልብስ

አገሪቷን የሚጎበኙ ቱሪስቶች በበረዶ በተሸፈኑ ተራራዎች፣ አረንጓዴ በሆኑ ሸለቆዎች፣ በወይን እርሻዎችና በመስክ ላይ በሚታዩ የተለያዩ ዕፀዋት ዓይናቸው መማረኩ አይቀሬ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ተራራ ላይ በምትገኘው በዚህች ትንሽ አገር 50 ዓይነት ኦርኪዶችን መስኩ ላይ ማየት እንችላለን። በተጨማሪም በሊክቴንስታይን ቤተ መዘክሮች፣ ቲያትር ቤቶችና የወይን መጥመቂያዎች ይገኛሉ። በመሆኑም በበጋም ሆነ በክረምት ቱሪስቶች ሊጎበኟት ይመጣሉ።

 የይሖዋ ምሥክሮች ከ1920ዎቹ ጀምሮ በሊክቴንስታይን ሲሰብኩ ቆይተዋል። በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ 90 ገደማ የሚሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች አሉ፤ እነሱም የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ለከተማዋ ነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ያስተምራሉ።