በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ንቁ! ቁጥር 4 2017 | ሥራ ይበዛብሃል?

በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች በጣም ሥራ ይበዛባቸዋል፤ በዚህም ምክንያት ከሌሎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ሊበላሽ እንዲሁም የቤተሰባቸው ሰላም ሊደፈርስ ይችላል።

ጊዜያችንን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

ጠቢቡ ንጉሥ ሰለሞን “ብዙ በመልፋትና ነፋስን በማሳደድ ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ ጥቂት እረፍት በማድረግ የሚገኝ አንድ እፍኝ ይሻላል” ሲል ጽፏል።—መክብብ 4:6

ይህ “ንቁ!” መጽሔት ጊዜያችንን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መጠቀም የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

 

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ሥራ ይበዛብሃል?

ብዙ ሰዎች ሥራቸውና የቤተሰብ ሕይወታቸው ያስከተለባቸውን ኃላፊነት በተሟላ ሁኔታ መወጣት አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ይህ የሆነው ለምንድን ነው? ይህን ችግር መፍታት የሚቻለው እንዴት ነው?

አስደናቂዋ አርክቲክ ተርን

አርክቲክ ተርን የተባሉት ወፎች በየዓመቱ ከአርክቲክ አካባቢ ተነስተው እስከ አንታርክቲካ በሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጉዞ 35,200 ኪሎ ሜትር የሚያክል ርቀት ይበራሉ ተብሎ ይታመን ነበር። ይህ ግን እነዚህን ወፎች አስደናቂ ካደረጓቸው ምክንያቶች አንዱ ብቻ ነው።

‘መልካም ስም ከብዙ ሀብት ይሻላል’

መልካም ስም ማትረፍ እንዲሁም የሌሎች ሰዎችን አክብሮት ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

ለቤተሰብ

ልጆች ራሳቸውን ችለው መኖር ሲጀምሩ

አንዳንድ ባለትዳሮች ልጆቻቸው አድገው ከቤት ሲወጡ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል። ወላጆች በዚህ ወቅት የሚሰማቸውን ስሜት ማሸነፍ የሚችሉት እንዴት ነው?

ቃለ ምልልስ

በአንጎል ላይ ጥናት የሚያካሂዱ አንድ ፕሮፌሰር ስለሚያምኑበት ነገር ምን ይላሉ?

ፕሮፌሰር ራጄሽ ካላርያ ሥራቸውንና የሚያምኑበትን ነገር በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። ስለ ሳይንስ ለማጥናት የተነሳሱት ለምንድን ነው? ‘ሕይወት የተገኘው እንዴት ነው?’ የሚለውን ጥያቄ መመርመር የጀመሩት ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ፈተና

አንድ ሰው በፈተና ሲሸነፍ ትዳሩ ሊፈርስ፣ ጤንነቱ ሊቃወስ፣ ሕሊናው ሊወቅሰው እንዲሁም ሌሎች አስከፊ መዘዞች ሊያስከትልበት ይችላል። ራስህን ከፈተና መጠበቅ የምትችለው እንዴት ነው?

ንድፍ አውጪ አለው?

የፖሊያ ቤሪ ደማቅ ሰማያዊ ቀለም

ፖሊያ ቤሪ በውስጡ ሰማያዊ ቀለም እንዲኖረው የሚያደርግ ንጥረ ነገር ባይኖረውም በየትኛውም ተክል ላይ የማይታይ ደማቅ ሰማያዊ ቀለም አለው። ታዲያ ይህን የመሰለ አስደናቂ ቀለም ሊኖረው የቻለው እንዴት ነው?

በተጨማሪም . . .

መጽሐፍ ቅዱስ ደስተኛ ቤተሰብ እንዲኖረኝ ሊረዳኝ ይችላል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ጥበብ ያዘሉ ምክሮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በቤተሰብ ሕይወታቸው ደስተኛ እንዲሆኑ ረድተዋቸዋል።

ሞኒካ ሪቻርድሰን፦ አንዲት የሕክምና ባለሙያ ስለምታምንበት ነገር ምን ትላለች?

‘ልጅ በሚወለድበት ወቅት የሚታየው አስገራሚ ክንውን እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?’ የሚል ጥያቄ ነበራት። በሕክምና ሙያዋ ያገኘችው ተሞክሮ ምን መደምደሚያ ላይ እንድትደርስ አደረጋት?