በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ንቁ!  |  ቁጥር 4 2016

 የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | ልማዶችህን መቆጣጠር የምትችለው እንዴት ነው?

2 አመቺ ሁኔታዎችን ፍጠር

2 አመቺ ሁኔታዎችን ፍጠር
  • አመጋገብህን ለማስተካከል ቆርጠሃል፤ ሆኖም አይስክሬሙን ስታይ ትፈተናለህ።

  • ማጨስ ለማቆም ወስነሃል፤ ይሁንና ጓደኛህ ውሳኔህን እያወቀ ሲጋራ ሰጠህ።

  • ከዛሬ ጀምረህ ስፖርት ለመሥራት ወስነሃል፤ ይሁን እንጂ ከቁም ሣጥንህ ውስጥ የስፖርት ጫማህን መፈለግ በራሱ ትልቅ ሥራ ሆኖብሃል!

ከላይ የተገለጹትን ሁኔታዎች የሚያመሳስላቸው ምን እንደሆነ ልብ ብለሃል? በተደጋጋሚ እንደታየው፣ ያለንበት ሁኔታና አብረናቸው ጊዜ የምናሳልፋቸው ሰዎች ጥሩ ልማዶችን ማዳበርም ሆነ መጥፎ ልማዶችን ማሸነፍ እንድንችል ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ብልህ ሰው አደጋ ሲያይ ይሸሸጋል፤ ተሞክሮ የሌለው ግን ዝም ብሎ ይሄዳል፤ መዘዙንም ይቀበላል።”ምሳሌ 22:3

መጽሐፍ ቅዱስ አርቀን እንድናስብ ይመክረናል። እንዲህ የምናደርግ ከሆነ ግባችን ላይ እንዳንደርስ እንቅፋት የሚሆኑ ሁኔታዎችን ማስወገድና ለግባችን መሳካት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንችላለን። (2 ጢሞቴዎስ 2:22) በአጭር አነጋገር፣ አመቺ ሁኔታዎችን መፍጠር የጥበብ አካሄድ ነው።

መጥፎ የሆነውን ማድረግ ከባድ እንዲሆንብህ፣ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ደግሞ ቀላል እንዲሆንልህ አድርግ

ምን ማድረግ ትችላለህ?

  • መጥፎ የሆነውን ማድረግ ከባድ እንዲሆንብህ አድርግ። ለምሳሌ ያህል፣ ለጤና የማይጠቅሙ ምግቦችን ማስወገድ የምትፈልግ ከሆነ እንዲህ ዓይነት ምግቦች ቤትህ ውስጥ እንዳይኖሩ አድርግ። ይህን ማድረግህ፣ እንዲህ ዓይነቱን ምግብ መብላት ቢያምርህም እንኳ ምግቡን ማግኘት ቀላል ስለማይሆን ጠቃሚ ያልሆነ ምግብ ከመብላት ትቆጠባለህ።

  • ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ቀላል እንዲሆንልህ አድርግ። ለምሳሌ ያህል፣ ጠዋት ከእንቅልፍህ እንደተነሳህ ስፖርት ለመሥራት ግብ ካወጣህ ማታ ከመተኛትህ በፊት የስፖርት ልብስህን አዘጋጅተህ እደር። ማዳበር የምትፈልገውን ልማድ መጀመሩ ቀላል እንዲሆንልህ ካደረግክ ይህን ልማድ ይዞ መቀጠሉ ብዙም አይከብድህም።

  • ጓደኞችህን በጥንቃቄ ምረጥ። ብዙውን ጊዜ አብረናቸው የምንሆነውን ሰዎች መምሰል ይቀናናል። (1 ቆሮንቶስ 15:33) ስለዚህ ልታስወግደው የምትፈልገውን ልማድ እንድትቀጥልበት ከሚያበረታቱህ ሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት ላይ ገደብ አብጅ፤ እንዲሁም ጥሩ ልማዶችን እንድታዳብር ከሚረዱህ ሰዎች ጋር ተቀራረብ።