የመንፈስ ጭንቀት ያለባቸው በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ እንደሆነ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ።

ይህን ችግር በተመለከተ ማድረግ የምንችለው ነገር ያለ ይመስልሃል?

ይህ “ንቁ!” መጽሔት በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች የመንፈስ ጭንቀትን መቋቋም የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ይጠቁማል፤ በተጨማሪም ወላጆች በመንፈስ ጭንቀት የሚሠቃዩ ልጆቻቸውን መርዳት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ አንዳንድ ምክሮች ይሰጣል።