በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ  |  ቁጥር 1 2016

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ስንሞት ምን እንሆናለን?

ሰዎች ምን ብለው ያምናሉ? ስንሞት ሌላ አካል ይዘን መኖራችንን እንደምንቀጥል የሚያምኑ አሉ፤ ሌሎች ደግሞ ሞት የሁሉ ነገር መጨረሻ እንደሆነ ይሰማቸዋል። አንተስ ምን ብለህ ታምናለህ?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ሙታን . . . ምንም አያውቁም።” (መክብብ 9:5) ስንሞት በሕይወት መኖራችን ያከትማል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • የመጀመሪያው ሰው አዳም ሲሞት ወደ አፈር ተመልሷል። (ዘፍጥረት 2:7፤ 3:19) በተመሳሳይም ሁሉም ሰው ሲሞት ወደ አፈር ይመለሳል።—መክብብ 3:19, 20

  • ሰዎች ሲሞቱ ከኃጢአታቸው ነፃ ይሆናሉ። (ሮም 6:7) አንድ ሰው ከሞተ በኋላ በኃጢአቱ ምክንያት አይቀጣም።

የሞቱ ሰዎች ዳግመኛ በሕይወት መኖር ይችላሉ?

ምን ትላለህ?

  • ይችላሉ

  • አይችሉም

  • እርግጠኛ አይደለሁም

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

‘ከሞት ይነሳሉ።’—የሐዋርያት ሥራ 24:15

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ሞትን ከእንቅልፍ ጋር ያመሳስለዋል። (ዮሐንስ 11:11-14) አንድን ሰው ከእንቅልፉ ቀስቅሰን እንደምናስነሳው ሁሉ አምላክም የሞቱ ሰዎችን ከሞት ያስነሳል።—ኢዮብ 14:13-15

  • የሞቱ ሰዎች እንደተነሱ የሚገልጹ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ሙታን እንደሚነሱ ጠንካራ ማስረጃ ይሆኑናል።—1 ነገሥት 17:17-24፤ ሉቃስ 7:11-17፤ ዮሐንስ 11:39-44