በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ  |  ቁጥር 5 2017

የጦር መሣሪያዎች በሙሉ ይጠፋሉ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

በምድር ላይ ሰላም የሚሰፍንበት ጊዜይመጣ ይሆን?

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

  • አዎ

  • አይ

  • ምናልባት

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

በኢየሱስ ክርስቶስ ግዛት ሥር “ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ [ማለትም ለዘላለም] ሰላም ይበዛል።”​—መዝሙር 72:7

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • ክፉ ሰዎች ከምድር ላይ ይወገዳሉ፤ ይህም ጥሩ ሰዎች “ብዙ ሰላም” አግኝተው ‘እጅግ ደስ እንዲላቸው’ ያደርጋል።—መዝሙር 37:10, 11

  • አምላክ ጦርነትን ሁሉ ያስወግዳል።—መዝሙር 46:8, 9

በአሁኑ ጊዜ እውነተኛ የአእምሮ ሰላም ማግኘት ይቻላል?

አንዳንዶች ምን ብለው ያምናሉ? መከራና የፍትሕ መዛባት በሞላበት ዓለም ውስጥ እውነተኛ የአእምሮ ሰላም ማግኘት እንደማይቻል የሚያምኑ ሰዎች አሉ። አንተስ ምን ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ከአምላክ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ያላቸው ሰዎች “ከመረዳት ችሎታ ሁሉ በላይ [የሆነውን] የአምላክ ሰላም” በአሁኑ ጊዜም እንኳ ማግኘት ይችላሉ።—ፊልጵስዩስ 4:6, 7

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • አምላክ መከራንና የፍትሕ መዛባትን በማስወገድ “ሁሉንም ነገር አዲስ [ለማድረግ]” ቃል ገብቷል።—ራእይ 21:4, 5

  • ‘መንፈሳዊ ፍላጎታችንን’ በማሟላት ውስጣዊ ሰላም ማግኘት እንችላለን።—ማቴዎስ 5:3 የግርጌ ማስታወሻ