በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

የምትወደውን ሰው በሞት ስታጣ

የምትወደውን ሰው በሞት ስታጣ

“የኔ ፍቅር . . . አምላክ የተሻለውን ነገር ስለሚያውቅ . . . በቃ አታልቅሺ።”

አንዲት ሴት ወደ ቤቤ ጠጋ ብላ ይህን ሐሳብ በጆሮዋ ሹክ አለቻት። በዚህ ወቅት ቤቤ፣ በመኪና አደጋ ሕይወቱ ባለፈው የአባቷ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ነበረች።

ቤቤ ከአባቷ ጋር በጣም ትዋደድ ነበር። መግቢያው ላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ በአሳቢነት ተነሳስታ የተናገረችው የቤቤ የቅርብ ወዳጅ ብትሆንም ንግግሩ ቤቤን ከማጽናናት ይልቅ ጎዳት። ቤቤ “አባባ ባይሞት ይሻል ነበር” እያለች ታጉተመትም ነበር። ከዓመታት በኋላ ቤቤ በጻፈችው መጽሐፍ ላይ ይህን ገጠመኝ ማውሳቷ በዚህ ጊዜም ቢሆን ሐዘኑ እንዳልወጣላት በግልጽ ያሳያል።

ቤቤ በራሷ ሕይወት እንደተመለከተችው፣ አንድ ሐዘንተኛ በተለይ ከሟቹ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ከነበረው ከሐዘኑ ለመጽናናት ረጅም ጊዜ ሊወስድበት ይችላል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሞት “የመጨረሻው ጠላት” ተብሎ መጠራቱ የተገባ ነው። (1 ቆሮንቶስ 15:26) ሞት ልንቋቋመው በማንችለው ሁኔታ ሕይወታችንን የሚያመሰቃቅልብን ከመሆኑም ሌላ አብዛኛውን ጊዜ ባልጠበቅነው ሰዓት በጣም የምንወዳቸውን ሰዎች ይነጥቀናል። ሞት ከሚያስከትለው ከባድ ጉዳት ማምለጥ የሚችል የለም። በመሆኑም የምንወደውን ሰው በሞት በማጣታችን የተነሳ ግራ ብንጋባ የሚያስገርም አይደለም።

ምናልባት እንዲህ የሚሉ ጥያቄዎች ተፈጥረውብህ ይሆናል፦ ‘ሐዘኑን ለመርሳት ምን ያህል ጊዜ ይፈጅብኛል? አንድ ሰው ከደረሰበት ሐዘን መጽናናት የሚችለው እንዴት ነው? ሐዘን የደረሰባቸውን ሰዎች ለማጽናናት ምን ማድረግ እችላለሁ? በሞት ያጣናቸው የምንወዳቸው ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?’