በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጠበቂያ ግንብ  |  ቁጥር 4 2017

በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ሰዎች ‘በብዙ ሰላም እጅግ ደስ ይላቸዋል።’—መዝሙር 37:11

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ጭንቀትን እንድትቋቋም ሊረዳህ ይችላል?

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

  • አዎ

  • አይ

  • እኔ እንጃ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ [በአምላክ] ላይ ጣሉ፤ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል።” (1 ጴጥሮስ 5:7) መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ከሚያስጨንቁህ ነገሮች ሁሉ እፎይታ እንድታገኝ ሊረዳህ እንደሚችል ማረጋገጫ ይሰጣል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • በጸሎት አማካኝነት ‘የአምላክን ሰላም’ ማግኘት ትችላለህ፤ ይህ ደግሞ ጭንቀትህን ለማቅለል ይረዳሃል።—ፊልጵስዩስ 4:6, 7

  • በተጨማሪም የአምላክን ቃል ማንበብ ውጥረት የሚፈጥሩ ሁኔታዎችን እንድትቋቋም ሊረዳህ ይችላል።—ማቴዎስ 11:28-30

ጭንቀት የሚወገድበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

አንዳንዶች ምን ብለው ያምናሉ? ጭንቀትና ውጥረት የሕይወታችን ክፍል እንደሆኑ አድርገው የሚያስቡ ሰዎች አሉ። ከጭንቀት የምንገላገለው ስንሞት ብቻ ነው ብለው ያምናሉ። አንተስ ምን ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አምላክ ለጭንቀት መንስኤ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ያስወግዳል። “ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”—ራእይ 21:4

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?